ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ወቅታዊ ዜናዎች፦
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ወቅታዊ ዜናዎች፦
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
በዚህ ገጽ አዳዲስ መሪዎችን ወደ አናንተ እናደርሳለን መልካም ንባብ
አይነ ስውሯ ቫንጋ - 3 ሺህ አመታትን አሻግራ ታያለች!
http://www.ethiotrick.page.tl on 01/12/2016 at 5:21pm (UTC)
 አይነ ስውሯ ቫንጋ - 3 ሺህ አመታትን አሻግራ ታያለች!...
.
- ከ20 አመት በፊት - ኦባማ ይመረጣል፣ 9/11 ይከሰታል፣
አይሲስ ይመጣል ብላለች
- አይሲስ አውሮፓን ይቆጣጠራል፣ ሰው እንደ አራዊት ይኖራል፣
በ5079 አለም ትጠፋለች ብላለች
- ከተናገረቻቸው ትንቢቶች፣ 85 በመቶው በገሃድ ተፈጽመዋል!
.
“የባልካኗ ኖስትራዳመስ” ሲሉ ይጠሯታል ብዙዎች፡፡
ገና የ12 አመት ልጅ ሳለች የአይኖቿን ብርሃን ያጣችው፣
ቡልጋሪያዊቷ ባባ ቫንጋ፣ በወጣትነቷ ነበር መጠንቆል፣ ባህላዊ
ፈውስ መስጠትና ትንቢት መናገር የጀመረቺው፡፡
ትንቢቶቿ በተግባር ሲፈጸሙ፣ ፈውሷ ብዙዎችን ማዳን ሲጀምር፣
ስሟ በሁሉም መጠራት ጀመረ፡፡
የአገር መሪዎች፣ ሳይንቲስቶችና የታሪክ አጥኝዎች ሳይቀሩ
የጥንቆላና የፈውስ ጥበቧ ቋሚ ተጠቃሚዎች መሆን ጀመሩ፡፡
የቡልጋሪያ ኮሙኒስት ፓርቲ መሪዎች ሳይቀሩ፣ ወደዚህች ሴት
ቤት በማምራት ምክሯን መቀበልና ትንቢቷን ሰምተው
አካሄዳቸውን ማስተካከል ያዙ፡፡
የአገሪቱ የደህንነት ጽህፈት ቤትም፣ ሴትዬዋ የአገርን መጻይ
እጣ ፋንታ ቀድማ የምታውቅ ታላቅ ነቢይና አማካሪ ናትና፣
ጥበቃ ያደርግላት ጀመር፡፡
ባባ ቫንጋ በዚህ መልኩ ለ50 አመታት ያህል ስትጠነቁል፣
ስትተነብይና ስትፈውስ ኖረች...
ኖረች ኖረችና...
እ.ኤ.አ በ1996 ከዚህ አለም በሞት ተለየች - በ85 አመት
ዕድሜዋ...
.
.
ከሰሞኑ...
ታላላቅ የአለማችን መገናኛ ብዙሃን፣ የዛሬ 20 አመት
ስለሞተቺው ባባ ቫንጋ አብዝተው መዘገብ ይዘዋል፡፡
ዘገባዎች እንደሚሉት...
በመቶዎች የሚቆጠሩ ትንቢቶችን የተናገረቺው ባባ ቫንጋ፣
ከትንቢቶቿ መካከል 85 በመቶው ተሳክቶላታል - ይሆናል ያለቺው
ሆኖ ታይቷል፡፡
ምን ምን አለች? ምን ምን ሆነላት?...
ዘ ሰን፣ ዘ ዴይሊ ሚረር፣ ሜትሮ፣ ዴይሊ ሜይልና ሌሎችም ስለ
ሴትዬዋ ካስነበቡት ያገኘሁትን እነሆ!...
.
.
የሴብቴምበር 11 ጥቃት
እ.ኤ.አ በ1989 ይህቺው ሴት አንድ ትንቢት ተናገረች...
“አስፈሪ!... እጅግ አስፈሪ ነገር ይሆናል!... የአሜሪካዎቹ
ወንድማማቾች በብረት ወፎች ተመትተው እንክትክታቸው
ይወጣል!... ተኩላዎቹ ቁጥቋጦ (bush) ውስጥ ተደብቀው
አምርረው ያለቅሳሉ፣ የንጹሃን ደም እንደ ጎርፍ ይፈስሳል!...”
በማለት፡፡
ይህን ንግግሯን የዘ ሰን ጋዜጣ ዘጋቢ እንዲህ ይፈታዋል...
“ቫንጋ ‘የአሜሪካዎቹ ወንድማማቾች’ ያለቻቸው፣ ሁለቱን የኒዮርክ
መንትያ ህንጻዎች ነው፡፡ የብረት ወፎች ስትል በምሳሌ
የገለጸቻቸው ደግሞ፣ አውሮፕላኖችን ነው፡፡ ቁጥቋጦ (bush)
ቡሽ ያለቺውም፣ የያኔውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽን
ነው፡፡ ይህ ሁሉ ተያይዞ ሲተረጎም፣ እ.ኤ.አ በ2001
በመንትያዎቹ ህንጻዎች ላይ የተቃጣውን የሽብር ጥቃትና እልቂት
ያመለክታል!...”
.
የበረዶ ጉዳይ...
በ1950ዎቹ ነበር የምድር ዋልታ የበረዶ ግግር ይቀልጣል፣
የውቅያኖሶች ሙቀት ይጨምራል ብላ የተነበየቺው፡፡ እሷ ይሄን
ካለች ከአስርት አመታት በኋላ ነው የአለም የሙቀት መጨመር
ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአገራትና የመንግስታት አጀንዳ መሆን
የጀመረው፡፡ የበረዶ ግግር መቅለጥና፣ ሙቀት መጨመሩን
የጀመረው፡፡
.
የኩርስክ መስጠም...
እ.ኤ.አ በ2000...
ኩርስክ የተባለቺዋ የሩስያ ግዙፍ የኒውክሌር መርከብ፣
በድንገተኛ የውቅያኖስ ማዕበል ተመታች፡፡ አለማቀፍ የአደጋ ጊዜ
ሰራተኞች፣ ኩርስክን ከጥፋት ለማዳን ደፋ ቀና አሉ፡፡
አልተሳካላቸውም!... መርከቧንም፣ በውስጧ የነበሩ ሰዎችንም
የባሬንትስ ባህር ሆድ በላቸው፡፡ ከፍተኛ ሃዘን ሆነ!...
እስከዚህ አሳዛኝ ክስተት ድረስ፣ ቫንጋ ከ20 አመታት በፊት
ስለተናገረቺው አንድ ትንቢት ነገሬ ብሎ ያሰበ ሰው አልነበረም፡፡
እሷ ግን ተናግራ ነበር...
እ.ኤ.አ በ1980፣ ቫንጋ ሀያ አመታትን ወደፊት አሻግራ
ተመለከተች፡፡ ተመልክታም እንዲህ አለች...
“ልክ ክፍለ ዘመኑ ሲቀየር (በነሃሴ 1999 ወይም በ2000)፣
ኩርስክን ውሃ ይበላታል!... መላው አለምም ስለዚህ አሳዛኝ
ክስተት አምርሮ ያለቅሳል!”
ይህቺው ጉደኛ ሴት...
በ2004 በፓሲፊክ ውቅያኖስ ዳርቻ የተከሰተውን ሱናሚ
በተመለከተም፣ ከሀያ አመታት በፊት ተናግራ ነበር...
“በታላቁ የባህር ዳርቻ ላይ ታላቅ ማዕበል ይነሳል፤ ህዝቡንና
ከተማዎችንም ይውጣል!” በማለት፡፡
.
“ኦባማ ይገዛል!... እሱም፣ የመጨረሻው ገዢ ይሆናል!...”
የቀለም ልዩነት በገነነበት፣ ጥቁሮች ለባርነት እንጂ ለመሪነት
ብቁ አይደሉም ተብሎ በሚታሰብበት፣ የዘር መድልዖ በነገሰበት
ዘመን...
ባባ ቫንጋ፣ ሲሰሙት ፌዝ የሚመስል ነገር ተናገረች...
“44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት፣ አፍሪካ አሜሪካዊ ይሆናል!...”
የሚል፡፡
ከረጅም አመታት በኋላ ግን፣ የሰሙት ሰምተው ያፌዙበት፣
ያልሰሙትም ቢሰሙት ይሳለቁበት የነበረው ይህ ንግግሯ፣
የሴትዬዋን የበቃች ነቢይነት ያረጋገጠ እውነት ሆኖ ተገኘ!...
“ይቻላል!...” የሚል መፈክር ይዞ የተነሳ፣ ባራክ ሁሴን ኦባማ
የተባለ ጸጉረ ከርዳዳ ሰው፣ የነጮች ብቻ ቤት ወደነበረው ነጩ
ቤት (ዋይት ሃውስ) ሰተት ብሎ ገባ!...
የቫንጋ የነጩ ቤት ትንቢት ግን በዚህ አያበቃም...
“ይህ ሰው፣ የመጨረሻው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነው!...”
ስትልም፣ ግራ የሚያጋባ ነገር አክላበታለች፡፡
“እዚህ ላይ ወራጅ አለ!...” እንበል እንዴ?...
.
የአውሮፓ መከራ እና ፍጻሜ!...
ከ10 ቀናት በኋላ፣ የፈረንጆች 2016 ይብታል!...
“ይህ አመት...” አለች ቡልጋሪያዊቷ ቫንጋ ከ30 አመታት በፊት፡፡
“ይህ አመት ለአውሮፓ የመከራ ነው!... የፍጻሜዋ
መጀመሪያ!...”
እንዲህ ነበር ያለቺው ቫንጋ...
“በ2016 አውሮፓ በሙስሊም ጽንፈኞች ትወረራለች፤
አውሮፓውያንም ክፉኛ ይደቆሳሉ!... ጽንፈኞቹ አውሮፓውያንን
በኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ክፉኛ እየደበደቡ፣ በመላ አህጉሪቱ
መስፋፋታቸውን ይቀጥላሉ!... የሚያቆማቸውም አይኖርም!...
እ.ኤ.አ እስከ 2025 አውሮፓውያን በሙሉ ድምጥማጣቸው
ይጠፋል፤ አውሮፓም ሰው አልባ ምድረ በዳ ትሆናለች!...
በስተመጨረሻም፣ በ2043 መቀመጫውን በሮማ አድርጎ
አውሮፓን አንቀጥቅጦ የሚገዛ እስላማዊ መንግስት
ይፈጠራል!...”
ቫንጋ በዚህም አላበቃችም...
“በዚህ አመትም፣ የአለም ኢኮኖሚ በሞላ በሙስሊሙ ቁጥጥር
ስር ይውላል!...” ብላለች፡፡
የዘ ሰን ጋዜጣ ዘጋቢ፣ ይሄን የሴትዬዋን ትንቢት ችላ
አላለውም...
“አለምን በሽብር እያመሰ ያለው ጽንፈኛው ቡድን አይሲስ፣
በሊቢያና በሶርያ ቁልፍ ከተማዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉና
ሃይሉን ማጠናከሩ፣ እንዲሁም ህዋሱን ወደ አውሮፓ አገራት
መዘርጋቱ፣ የሴትዬዋ ትንቢት ሳይዝ አይቀርም ያሰኛል...” ሲል
አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
.
የአሜሪካ ክርስትናን የመመለስ ጥረት
ይሄው ሌላ የሴትዬዋ ትንቢት...
“እ.ኤ.አ በ2066... አሜሪካ አዲስ የአየር ንብረት ለውጥ
መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ታውላለች፡፡ ይህን
የምታደርገውም፣ ሮምን ከእስላማዊው መንግስት ለመንጠቅና
ክርስትናን ወደ አውሮፓ ለመመለስ በማሰብ ነው!...”
እሷ እንደምትለው...
ይህ በሆነ በ16 አመቱ፣ ኮሙኒዝም ዳግም ወደ አውሮፓ እና
ወደተቀረው አለም ይመለሳል!...
.
የእሷ ትንቢት አያልቅም!...
በ2084 - ተፈጥሮ ዳግም ትወለዳለች!
በ2170 - እጅግ አስከፊው ድርቅ አለምን ይመታታል!
በ2480 - ሁለት ሰው ሰራሽ ጸሃዮች እርስ በእርስ ተጋጭተው፣
አለም በድቅድቅ ጨለማ ትዋጣለች!...
በ3005 - ማርስ ላይ የሚደረግ ሃያል ጦርነት፣ የፕላኔቷን
አቅጣጫ ይቀይረዋል፡፡
በስተመጨረሻም...
በ3797 - የሰው ልጅ ስልጣኔ እየተራቀቀ ሄዶ፣ ወደ ሌላ ሶላር
ሲስተም ሄዶ ህይወቱን መቀጠል የሚችልበት ደረጃ ላይ
ይደርሳል፡፡ አንዳንዶች ወደ ሌላ ፕላኔቶች ሄደው ሲያመልጡ፣
የቀረው በምድር ላይ ያለ ፍጡር ሁሉ ይሞታል!...
.
ዘ ሰን እንዲህ ብሎ ቢያበቃም...
ዘዴይሊ ሚረር ግን የሴትዮዋን ትንቢትም፣ የአለምን ታሪክም
ያስቀጥለዋል...
በ2341 - ተደጋጋሚ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች
ይከሰቱና፣ መሬትን ለኑሮ የማትመች ያደርጓታል፡፡ የሰው ልጅ ወደ
ሌላ ሶላር ሲስተም ያመልጣል፡፡ ይሄም ሆኖ ግን የሃብት እጥረት
ከመኖሩ ጋር በተያያዘ፣ እጅግ የከፋ ጦርነት ይሆናል!...
ከ3815 እስከ 3878 - ስልጣኔ ድምጥማጡ ይጠፋል!... የሰው
ልጅም እንደ አራዊት መኖር ይቀጥላል!... በኋላ ላይ ግን፣
አዲስ ሃይማኖት ይመጣና፣ የሰው ልጅን ከጨለማ ያወጣዋል!...
ከ4302 እስከ 4674 - “መጥፎ” እና “ጥላቻ” የሚባሉት
ሃሳቦች ሙሉ ለሙሉ ይጠፋሉ!... የሰው ልጅ በሞት የማይረታ
ህያው ፍጡር ይሆናል!... በህዋው ውስጥ ተበታትኖ የሚኖረው
ህዝብ፣ ከፈጣሪ ጋር መነጋገር ይጀምራል!...
.
እንዲህ እንዲህ ብሎ...
በ5079 - የአለም መጨረሻ ይሆናል!...
.
በዚህ መስመር - የሴትዬዋ ጉዳይ መጨረሻ ይሆናል!
ምንጭ ፦ learnhowtogetgirl.blogspot.com
ፀሐፊ ዮናስ ብርሀኑ
 

<-Back

 1 

Continue->

This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free