ራሰ በራነት ምንድን ነው? መነሻው እና ህክምናው
ምንድን ነው?
(በዳንኤል አማረ) "ፀጉር በማንኛውም የሰውነታችን
ቆዳ ላይ
ከእጃችን መዳፍ እና ከእግራችን ሶል ዉጪ
ይበቅላል ነገር ግን አብዛኛዎቹ ፀጉሮች ስስ ስለሆኑ በአይናችን ላናያቸው እንችላለን፡፡ ፀጉር ኬራቲን
(keratin) ከሚባለው ፕሮቲን በዉጨኛው የቆዳ
ክፍል የፀጉር ፎሊክል ዉስጥ ይሰራል፡፡ ፎሊክላችን
አዲስ የፀጉር ሴል ሲሰራ/ሲያመርት አሮጌ ሴሎቻችን
በአመት 6 ኢንች ወደ ዉጪ ቆዳችን ተገፍተው
ይወጣሉ የምናየው ፀጉር የሞተ ክር መሳይ ኬራቲን ሴል ነው፡፡ በአማካይ የአንድ አዋቂ ሰው ጭንቅላት
ከ 100,000-150,000 የሚደርስ ፀጉር ሲይዝ በቀን
100 ፍሬ ፀጉር በራሳቸው ጊዜ ይነቀላሉ
በማበጠሪያች ውስጥ ትንሽ የተነቀሉ ፀጉር ማግኝት
የተለመደ እና ሊያስደነግጠን የማይገባ ጤናማ
ሁኔታ ነው፡፡
|