የናት ውለታዋ የናት ውለታዋ ባወሳ እወዳለሁ
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመነፈሷ
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ ዘጠኝ ወር በሆዷ ከዛም በጀርባዋ
ጡታቷን እያጠባች እኔን ማሳደጏዋ
ዘወትር ይሰማኛል የናቴ ድካሟ
ጥራ በማሳደግ በሴትነት አቅሟ የናት ውለታዋ ባወሳ እወዳለሁ
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመነፈሷ
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ አባቴ ሞቶብኝ በህፃንነቴ
ደክማ አሳደገችኝ ብቻዋ እናቴ
ሳይርበኝ ሳይጠማኝወይም ሳልታረዝ
ነው ያሳደገችኝ እማም.........? የናት ውለታዋ ባወሳ እወዳለሁ
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመነፈሷ
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ የናት ውለታዋ ባወሳ እወዳለሁ
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመነፈሷ
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ እናቱን የማይወድ ሰው አለ ቢሉኝ
ሰው ነው አልለውም አውሬ ነው ባይ ነኝ
የዋሂቷ እናቴ እኔን ወላዲቷ
እጅጋ ይሰማኛል እውነተኛ ነቷ የናት ውለታዋ ባወሳ እወዳለሁ
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመነፈሷ
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ
|