ለማን ብዬ የሚለውን ምርጥ ሙዚቃ
ይጋበዙልን
ማነው ያለው? አልልም አልጠይቅም
ማነው ያለው? ብዬም አልጨነቅም ማነው ያለው? ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ
ማን ነው ያለው? ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም
ማን ነው ያለው? ውስጤ እንዳያውቀው ማንም
ማን ነው ያለው? ስቆ ማለፍ መተው ነው
የሚያኖርም የሰራም ደግ አባት ነው ለማን ብዬ ባዶነት ለሞላው
ለማን ብዬ ለገለባው ክብሬ
ለማን ብዬ ካበደው ጋር ልበድ
ለማን ብዬ ከጠፋው አብሬ
ለማን ብዬ እልህ ተጋብቼ
ጨካኝ ልሁን መራራቴን ትቼ ለማን ብዬ ባልተረጋገጠ
ለማን ብዬ መሬት ባልረገጠ
ለማን ብዬ በደለበ ወሬ
ለማን ብዬ በወለደ በሬ
ለማን ብዬ ስጦታው ሰላሜን
ለማን ብዬ ልነጠቅ ደስታዬን ማነው ያለው?
ካልኩኝ ብዙ እሰማለሁ
ማነው ያለው?
ብልስ ማንን አምናለሁ
ማነው ያለው?
አውቀዋለሁ ባይ ብዙ በሞላበት ያደክማል ጓዝ መዘዙ…
ራሱን ክቦ ለክብር ዝና
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ
እንዴት ይገፋል ይሄ ተጨምሮ
ሰው ለቁርሱ፣ እጁን አጣጥፎ ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ
ሲነግሩሀ ቢዋል ሳታምን ግባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ አሉ ተባለን ሳታምን ግባ
ማነው ያለው? አልልም አልጠይቅም
ማነው ያለው? ብዬም አልጨነቅም
ማነው ያለው? ምን አሉኝ ደግሞ ብዬ
ላልቆም ነገር ከመንገድ ከጉዞዬ
ማን ነው ያለው? ብዬ እኔ ሰው አልወቅስም ማን ነው ያለው? ውስጤ እንዳያውቀው ማንም
ማን ነው ያለው? ስቆ ማለፍ መተው ነው
የሚያኖርም፣ የሰራም ደግ አባት ነው
ለማን ብዬ አለኝ ያሉት በምድር
ለማን ብዬ ፈጥኖ ለሚያሳፍር
ለማን ብዬ ከዘመኔ ስፍር ለማን ብዬ ቅንጣት ለማልጨምር
ለማን ብዬ ወዳጅ ላፍራ ብዬ
የሰው ላድምቅ የኔን ቀን ገድዬ
ለማን ብዬ ቃላት ከማይመርጠው
ለማን ብዬ ለከት ላጣ አንደበት
ለማን ብዬ ከማይጠቅም ምክር ለማን ብዬእርግማን ካለበት
ለማን ብዬ የኮከብ ድምቀቴን
ለማን ብዬ ላጥፋው ማንነቴን
ራሱን ክቦ ለክብር ዝና
ይራመዳል ሰው በሰው ጎዳና
ሞልቶ ላይሞላ ለሽንቁር ኑሮ እንዴት ይገፋል ይሄ ተጀምሮ
ሰው ለቁርሱ፣ እጁን አጣጥፎ
ጫፍ ይዞ መሄድ ሆዱን ታቅፎ
ላላዩት እውነት አሉ ላይረባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ ሲነግሩሀ ቢዋል ሳታምን ግባ
ሲነግሩሀ ውለው ሳትሰማ ግባ
አሉ ተባለን ሳታምን ግባ
|