ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ብልጭታና መብረቅ
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ብልጭታና መብረቅ
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
=> ሰውየውና እባቡ
=> አጌንጋና በቆሎው
=> አቡ ናዋስ እና ቃዲው
=> የውሻ ፀብ
=> ሌላ የቀበሮ ታሪክ
=> የተረገመች የእንጀራ እናት
=> ሞኙ ባልና ብልኋ ሚስት
=> ብልጭታና መብረቅ
=> ስስታም አትሁን
=> እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
የነጎድጓዳማ ዝናብ መንፈስ በጉ ስለጠፋበት ፍለጋ በወጣ ጊዜ እጅግ በጣም እየዘነበ በጉን በፍለጋ ላይ ሳለ የነጎድጓዱ መንፈስ ከአንዲት እንሽላሊት ዘንድ ይደርስና የጠፋበትን በግ አይታ እንደሆነ ጠየቃት፡፡ እርሷም “አይ! አላየሁትም፡፡ በዝናቡ ምክንያት በጣም በርዶኝ ስለነበረ ፀሃይ እየሞኩ ነበር፡፡” ብላ መለሰችለት፡፡ እርሱም “ታዲያ ምን ትመክሪኛለሽ? የጠፋብኝንስ በግ እንዴት ላገኘው እችላለሁ? ማንስ ይሆን የሰረቀው?” ብሎ ጠየቃት፡፡ እንሽላሊቷም “ግንደ ቆርቁር ጋ ሄደህ እርሷ የምታውቀውን ትነግርሃለች፡፡” አለችው፡፡ ነጎድጓዱም ወደ ግንደ ቆርቁር ሄዶ “በጌ ጠፍቶብኛልና አይተሽዋል?” ብሎ ጠየቃት፡፡ ግንደ ቆርቁሯም “እኔ የተለመደ ሥራዬን እየሠራሁ፣ እየቆረቆርኩ ነበርና በግህን አላየሁትም፡፡” አለችው፡፡ እርሱም “እናስ ታዲያ የጠፋብኝን በግ እንዴት ላገኘው እችላለሁ?” አላት። እርሷም “እስኪ ወደ እስስት ዘንድ ሂድ ። ሌሎች እንስሳትን ባየ ጊዜ የሚደበቀው አንዳች ክፉ ነገር ቢሠራ ነው። በፀፀት ምክንያት፡፡” አለችው፡፡ ነጎድጓዱም “በርግጥ የተደበቀበት ምክንያት ገብቶኛል፤በጌን ሠርቆት ወይም መርዞት መሆን አለበት፡፡” ብሎ አሰበ፡፡ ይህንንም ካለ በኋላ ወደ እስስት ዘንድ በማምራት እስስቱ ዘንድ እንደደረሰ “በል ና ውጣ ፣አንተ እስስት!” ብሎ ቢጣራም እስስቱ ከአንድ ዛፍ ስር ተደበቀ፡፡ ነጎድጓዱም እስስቱን ፍለጋ ከዛፉ ጀርባ ቢዞርም እስስቱ ግን ጫካው ውስጥ ገብቶ ተደበቀ፡፡ ሆኖም በመጨረሻ ነጎድጓዱም እስስቱን አግኝቶ “በጌን የሰረቅኸው አንተ ነሃ! በልተኸው ወይም መርዘኸው ይሆናል፡፡” ብሎ ነጎድጓዱ እስስቱን ሰነጣጠቀው፡፡ አስከዛሬም ድረስ ነጎድጓዳማ መብረቅ በመጣ ጊዜ በሽማሌዎች ዘንድ “ወደ ውጪ ወጥታችሁ ዛፍ ስር አትቁሙ፤ ምክንያቱም መብረቁ በጉን የሰረቀበትን እስስት እየፈለገ ነው፡፡” የሚል ብሂል አለ፡፡ የዚህም ተረት መልዕክት ክፉ ነገሮችን ሰርተው እንደሚደበቁ ሰዎች አትሁኑ የሚል ነው፡፡
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free