ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - አጌንጋና በቆሎው
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - አጌንጋና በቆሎው
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
=> ሰውየውና እባቡ
=> አጌንጋና በቆሎው
=> አቡ ናዋስ እና ቃዲው
=> የውሻ ፀብ
=> ሌላ የቀበሮ ታሪክ
=> የተረገመች የእንጀራ እናት
=> ሞኙ ባልና ብልኋ ሚስት
=> ብልጭታና መብረቅ
=> ስስታም አትሁን
=> እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
ከእለታት አንድ ቀን አጌንጋና ኦሜት የተባለው ጓደኛው ጋንቤላ ውስጥ ወደሚገኘው ፒኒኬው ወደተባለ መንደር አብረው ሄዱ፡፡ ከመንደሩም እንደደረሱ በጣም እርቧቸው ስለነበር ፒኒኬው ውስጥ በሚገኝ አንድ የቤተሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተስተናገዱ፡፡ ሰዎቹም በጣም መራባቸውን ባዩ ጊዜ ያልተቀቀለ በቆሎ እሸት ሰጧቸው፡፡ እነርሱም ይህን እሸት በቆሎ እንዴት ልናበስለው እንችላለን ከተባባሉ በኋላ ኦሜት “እስኪ እኔ እንዴት እንደምናበስለው መንገድ ልፈልግ፡፡” አለ፡፡ የማገዶ እንጨት አልነበራቸውም፣ ቁጥቋጦም አልነበረም፣ እንዲሁም ዛፎቹ ሁሉ ከወንዙ ባሻገር ነበሩ፡፡ ባረፉበት አካባቢ ዙሪያውን ለከብቶች መጠበቂያ አጥር የታጠረበት መቃብር ነበር፡፡ ኦሜትም በዚሁ መቃብር ስፍራ በመሄድ ከአጥሩ ላይ እንጨት በመምዘዝ ለበቆሎ ማብሰያ አመጣ፡፡ ሰዎቹም እንጨቱን እየሰበረ ባዩት ጊዜ እንዲህ እያሉ ጮሁበት “ልጃችንን የገደለውን ቡዳ አገኘነው፤ አሁን ደግሞ ነፍሱን ሊገድል በድጋሚ የመጣው በቀብሩ ስነ ስርአት ወቅት መሬቱን የመደልደሉ ስራ እስካሁን ስላልተጠናቀቀ ነው፡፡” በዚህን ጊዜ አጌንጋ የጓደኛውን ሕይወት ለማዳን በማሰብ ኦሜትን ሄዶ ከያዘው በኋላ በመደባደብ ተያይዘው ወደቁ፡፡ ሰዎቹም በመጡ ጊዜ አጌንጋ እንዲህ አለ “ተመልከቱ እዚህ ይዤ የመጣሁት የአእምሮ በሽተኛ ሰው ነውና አትጉዱት፡፡” ሰዎቹም ይህንኑ ሰምተው በመጨረሻ ዝም ካሉ በኋላ ሁለቱ ጓደኛማቾች እንዴት እንደተራቡ አይተው በቆሎዋቸውን ያበስሉ ዘንድ አጥሩ ላይ ያለውን እንጨት እንዲጠቀሙ ፈቀዱላቸው፡፡
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free