ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - የተረገመች የእንጀራ እናት
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - የተረገመች የእንጀራ እናት
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
=> ሰውየውና እባቡ
=> አጌንጋና በቆሎው
=> አቡ ናዋስ እና ቃዲው
=> የውሻ ፀብ
=> ሌላ የቀበሮ ታሪክ
=> የተረገመች የእንጀራ እናት
=> ሞኙ ባልና ብልኋ ሚስት
=> ብልጭታና መብረቅ
=> ስስታም አትሁን
=> እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
አንዲት ስምንት ወንድ ልጆችና አንድ ኮሬ የተባለ የእንጀራ ልጅ የነበሯት ሴት ነበረች፡፡ ኮሬ በጣም ጀግና ስለነበር ከጦር ሜዳ ምርኮኞች ይዞ ይመጣ ነበር፡፡ በዚህ ጀግንነቱ ስምንቱ ወንድማማቾች ይቀኑበት ነበር፡፡ እንዲገደልም ይፈልጉ ነበር፡፡ እርሱ ግን ማንም ረዳት የለውም ነበር፡፡ ስምንቱም ወንድማማቾች እንደርሱ ጀግና አለመሆናቸው እንደማያስደስታቸው ለእናታቸው ነገሯት፡፡ ወዲያውም “ለምን አናስወግደውም?” ብለው ጠየቋት፡፡ እርሷም “መልካም! እንግዲያው ወደጫካ ልኬው በዝሆን እንዲበላ አደርጋለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡ “ይህንን ማድረግ ትችያለሽ?” ሲሏት “አዎን እችላለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡ ከዚህ በኋላ እናትየው ኮሬን “ልጄ ሆይ! ስለታመምኩ መድኃኒት እንድታመጣልኝ እፈልጋለሁ፡፡” አለችው፡፡ እርሱም “ምን ዓይነት መድኃኒት?” ብሎ ጠየቃት፡፡ “የዝሆን ጭራ!” ብላ መለሰች፡፡ ኮሬም በጣም ጀግና ስለነበረ ዝሆን ገድሎ ጭራውን ይዞላት መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ እናትየውና ስምንቱ ወንድ ልጆቿ በኮሬ አለመበላት በጣም ተበሳጭተው ሊያስወግዱት ሌላ ዘዴ መዘየድ ጀመሩ፡፡ እናትየውም “አሁን ደግሞ እኔ ከወንዝ ውሃ ይዞልኝ እንዲመጣ ስልከው እናንተ አድፍጣችሁ ውሃ ውስጥ ወርውራችሁት ይሙት፡፡” አለቻቸው፡፡ ከዚያም ኮሬን “አሞኛልና በአስቸኳይ ውሃ ያስፈልገኛል፡፡” አለችው፡፡ ቀኑ መሽቶ ነበር፡፡ እርሱም ውሃውን ሊያመጣ ሲሄድ ወንድማማቾቹ ሊገድሉት ጦር ይዘው መጡበት፡፡ እርሱም ከጥቃታቸው አምልጦ አንድ በአንድ ገደላቸው፡፡
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free