ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
=> ሰውየውና እባቡ
=> አጌንጋና በቆሎው
=> አቡ ናዋስ እና ቃዲው
=> የውሻ ፀብ
=> ሌላ የቀበሮ ታሪክ
=> የተረገመች የእንጀራ እናት
=> ሞኙ ባልና ብልኋ ሚስት
=> ብልጭታና መብረቅ
=> ስስታም አትሁን
=> እናት ቀበሮና አያ ጅቦ
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
አንዲት ሁለት ግልገሎች የነበሯት ቀበሮ ነበረች፡፡ አንደኛውን ልጇን ወይናይ ብላ ሰየመችው፡፡ (ይህም ማለት እምብዛም ያልፈካና እምብዛም ያልጠቆረ ማለት ነው፡፡) ቀበሮዋም ምግብ ፍለጋ ስትሄድ ግልገሎቿን ዘግታባቸው ትሄድ ነበር፡፡ የሌላኛው ግልገል ስም ጌላ ነበር፡፡ ቀበሮዋም ወደቤቷ ስትመለስ እንዲህ ትላለች፤ “አንድ ወይናይ አንድ ጌላ በሩን ክፈቱልኝ፡፡” ታዲያ አንድ ቀን ቀበሮዋ ልጆቿን ስትጣራ አያ ጅቦ ይሰማና ቀበሮዋ ወደ አደን ስትሄድ እናታቸውን አስመስሎ ጠራቸው፡፡ ግልገሎቹ ግን ድምፁ ስለተለየባቸው ተጠራጠሩ፡፡ በዚህ ግዜ ጅቡ ድምፁን የበለጠ አቅጥኖ የጥሪ ቃላቱን ሲደግም እናታቸው መስላቸው በሩን ሲከፍቱ ጅቡ በላቸው፡፡ ቀበሮዋም ወደቤቷ ተመልሳ በተለመደ ድምጿ ልጆቿን ብትጣራ መልስ አጣች፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥም ዘላ ስትገባ ግልገሎቹ በጅቡ እንደተበሉ አወቀች፡፡ በሚቀጥለው ቀን ታዲያ ቀበሮዋ ጉድጓድ አዘጋጅታ ጉድጓዱን በፍየል ቆዳ ከሸፈነችው በኋላ ጅቡን አንዲት በግ ከእርሷ ጋር ተካፍሎ እንዲበላ ጋበዘችው፡፡ “ና ብላ፡፡” ብላ ስትጠራው ጅቡ በመጣ ጊዜ “የፍየሉ ቆዳ ላይ ተቀመጥ፡፡” አለችው፡፡ ነገር ግን ጅቡ የፍየሉ ቆዳ ወደጉድጓዱ ውስጥ በመጠኑ ጎድጎድ ማለቱን አየ፡፡ ቀበሮዋ ግን “ኧረ ምንም አይደል! እዚያ ተቀመጥ፡፡” ስትለው አያ ጅቦ ቆዳው ላይ ሲቀመጥ ወደ ጉድጓዱ ውስጥ በወደቀ ጊዜ ቀበሮዋ የፈላ ውሃ ጨምራበት ሞተ፡፡
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free