ንጉስ ሐይለስላሴ በአለም የፖለቲካ
መድረክ ንጉስ
ሐይለስላሴ ዝናን
አትርፈዋል
ኢትዮጵያንም
አስተዋውቀዋል። በአመራር ዘመናቸው
ስለጥቁሮች ነፃ
መውጣት
ታግለዋል። አፍሪካ
ከቅኝ ገዚዎች እጅ
እንድትወጣ ሲታገሉ የቆዩና የአፍሪካ
አንድነት ድርጅት
እንዲ ቋም ካደረጉት
መሪዎች አንዱም
ናቸው። ፕሬዘዳንት
ማንዴላ አገራቸውን ከአፓርታይድ ነፃ
ለማውጣት ትግል
በጀመሩ ጊዜ በድብቅ
በኢትዮጵያ
የውትድርና ስልጠና
እንዲያደርጉ ያደረጉት እኝሁ
ንጉስ ሐይለስላሴ
ነበሩ።
|