እዉነተኛ የፍቅር ታሪክ
በጣም ሚዋደዱ ሁለት ፍቅረኞች
ለመጋባት ይወስናሉ፡፡ቀለበት
ሊያስሩ ጥቂት ወራት ሲቀራቸዉ
ልጅቱ የመኪና አደጋ ይደርስባት እና ፊቷ ሙሉ በሙሉ ተበላሸ፡፡‹ቀሪ ሂወቴን መልከ-ጥፉ
እና አስጠሊታ
ሁኘ መኖሬ ግድ ሁኗል፡፡ከእንግዲህ
ላንተ የምገባ ሴት አደለሁም ፡፡ሌላ
ቆንጆ ወጣት ሴት ፈልገህ አግባ፡፡›
ብላ ለልጁ ፃፈችለት፡፡ከጥቂት ቀናት በኋካ እንዲህ ሚል ደብባቤ ደረሳት‹ዉዴ ማፈር
ያለበት ሰዉ ካለ
እኔ ነኝ ማፈር ያለብኝ፡፡በአይን
ህመም ምክንያት ማየት
እንደማልችል ዶከረተር ነግሮኛል፡፡
እንዲህ ሁኘ የ ምታገቢኝ ከሆነ እኔ አንቺን ለማግባት እፈልጋለሁ ፡፡› ወዲያዉ ተጋቡ
፡፡ልጁ ጭራሽ
ማየት አይችልም ነበር፡፡ለ 20
አመታት በፍቅር በደስታ
በመተሳሰብ ኖሩ፡፡እሷ የአይኑ
ብርሃን ሁና እየመራችዉ ፍቅራቸዉ ፈክቶ በሃሴት ኖሩ፡፡ከ20 አመት ቆይታ በኋላ ሴቷ
በጠና ታመመች፡፡
በባዶ ጨለማ ትቸዉ ልሞት ነዉ
ካለኔ ማን አለዉ እያለች ትጨነቅ
ነበር ፡፡ሞት አይቀርምና ወደ
ማይቀርበት አለም ሄደች፡፡ሚስቱ የሞተችበት እለት ሰዉየዉ አይኑን ገልጦ ማየት
ጀመረ፡፡ሰዉ ሁሉ
ተገረመ ‹አይነ ስዉር አልነበርኩም
የተበላሸዉን ፊቴን አየብኝ ብላ
እንዳትሳቀቅ ብየ ነዉ አይነ ስዉር
መስየ የኖርኩት፡፡›አለ፡፡ የታሪኩ ‹ሞራል› እዉነተኛ ፍቅር አካላዊ ዉበትን
ሳይሆን
ሚመለከተዉ ዉስጣዊ ዉበትን
ነዉ፡፡ምክንያቱም እዉነተኛ ፍቅር
በአይን ሳይሆን በልብ ነዉ
ሚመለከተዉ፡፡
|