አባ ገስጥ(ራስ አበበ አረጋይ)፤ተጉለት/ሸዋ
"የዘመናዊውም ዓለም ታላቅ የጦር ጅግና" ( የወቅቱ
የእንግሊዝ ጦር አዛዥ የተናገሩት)
ራስ አበበ አረጋይ በሰሜን ሸዋ ተጉለት ውስጥ
ሲያደብርና ዋዩ በሚባል ቦታ ተወለዱ። ልዑል ራስ
አበበ አረጋይ የቤተክርስቲያንና ዘመናዊ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን፤የክቡር ዘበኛ ሰራዊት አባል
ሆነው ሚሊታሪ ሳይንስ በማጥናት በመጀመሪያ
የሌተናንት ቀጥሎም የካፕቴንነት ማዕረጎችን
ተቀብለዋል።ከጦርነቱ ድል በኋላም በጦር
ሚንስትርነት ማእረግ ተሸመዋል።
ልዑል ራስ አበበ አረጋይ በ1928 ዓ. ም ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የአዲስ አባባ ከተማ
ፖሊስ አዛዥ ነበሩ። በወቅቱ ፋሽስት ኢጣሊያ ከ40
ዓመት በፊት አድዋ ላይ በኢትዮጵያውያን
የደረሰባትን አሳፋሪ ሽንፈት ለመበቀል በማይጨው
ጦርነት ላይ የተጠቀመቸው በአውሮፕላን የሚረጭ
የመርዝ ጋዝ በመሆኑና ከጠላት ጋር አብረው የነበሩት የትግራይ ባንዳዎች ለጣልያን የኢትዮጵያን ምስጢር
ይሰጡ ስለነበር በጦርነቱ የወገን ጦር ክፉኛ
በመጎዳቱ ንጉሱን ጨምሮ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ግድ
ሆነ።
ከማይጨው ጦርነት በኋላ ጠቅላላ ወታደሩ ወደ
ሽምቅ ውጊያ ለመግባት ተገደደ። የራስ አበበም እምቢ "ለሀገሬ" የሚለው የአርበኝነትና የጀግንነት
ውሎ የሚጀምረው ከዚህ ነው።ራስ አበበ አረጋይ
የኢትዮጵያን የነፃነት ሰንደቅ ዓላማ አንግበው
አምስት ዓመት ሙሉ በሰሜን ሸዋ (በዱር
በገደል)የኢትዮጵያን ሽምቅ ተዋጊዎች በመምራትና
የጣሊያን ወራሪ ኃይል አሳፍረው በመመለስ ትልቅ ጀብዱ በመፈጸም ከስድስት ጊዜ በላይ ቆስለው
የተረፉት ጥፈት እንደበዛበት እላቂ አቡጀዴ
ሰውነታቸው በጠባሳ ተሞልቶ ነበር።
ከአምስት ዓመት አርበኝነት ተጋድሎ በኋላ
የፋሽስቱ ወራሪ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተጠራርጉ
ከኢትዮጵያ ሲለቅ ስደት ላይ የነበሩት አጼ ኃይለሥላሴ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ወደ
አዲስ አበባ ተመልሰዋል። በወቅቱ ልዑል ራስ አበበ
አረጋይና በሌሎችም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች
ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።
በሌላ ጊዜ፤በአምስቱ አመት አርበኝነት ዘመን፡
ከአንድ ቤት ከወጡት አምስት ወንድማማቾችና በመትረየስና በቦንብ ፍንጣሪ ተበሳስተው ሁለቱ
ብቻ ለጉድ የተረፉትን፤የሸንቁጥ ልጆች(መራቤቴ|
ሸዋ)ገድል ይዤ እመጣለሁ፡፡
|