ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - እናታችን አሸባሪ ናት
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - እናታችን አሸባሪ ናት
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
=> ከዴርቶ ጋዳ የተወሰደ
=> እናታችን አሸባሪ ናት
=> የደብሪቱ ወተት
=> የመጨረሻው ኑዛዜ
=> ፍለጋ
=> ”እናቴ አልዳነችም! ...
=> ከባህር የወጣች አሳ
=> ጭለማና ብርሀን
=> ሠላማዊ ህልም
=> የዕብደት ዋዜማ
=> የአስከሬኑ ሳጥን የመጨረሻ ሚስማሮች
=> ሁለት ፅንፎች
=> ከስሜት መፋታት! Written by ደራሲ - ጁሊ በርግማን ትርጉም- ኢዮብ ካሣ
=> ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያስለቅሳል . . .
=> ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
=> love
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
አባቴ ስድስት ልጆቹን ሰበሰበና የመረረ ነገር ሲኖር ብቻ የሚጠቀምበትን ሰማያዊ ሽፋን ያለውን አጀንዳውን ፊቱ ዘርግቶ ስብሰባውን ከፈተ (ስለዚህ አጀንዳው ሌላ ቀን በሰፊው እና ወራለን)! ገና ከመጀመሪያው የእለቱን አጀንዳ ሲያስተዋውቅ ነበር ሁላችንም የደነገጥነው ‹‹ ወ/ሮ ማንያህልሻል ተክሌን የሚመለከት ነው ›› ሲል ግራ ተጋባን ...... የእናታችን ስም እንዲህ እንደባቡር ሃዲድ ረዝሞ ያውም በአባታችን ሙሉውን ሲጠራ ሰምተን አናውቅም! ማኑየ ....የኔገላ ....ወለላየ ነበር በደጉ ቀን ሲጠራት! ሌላው ያጨናነቀን ነገር አባባ የእናታችንን ስም እንዲህ ያራዘመ ዋናውን ጉዳይማ እስከ ነገወዲያም አይጨርሰው የሚል ስጋ ትነበር! ‹‹ያው እንግዲህ ይሄ ቤተሰብ እስከ ሚመጣው የፋሲካ በአል መካከለኛ የበአል አከባበር ካላቸው ቤተሰቦች ተርታ ይሰለፍ ዘንድ ቀን ተሌት እየለፋና እየደከመ መሆኑ ከእናተ አይደበቅም! እንግዲህ በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ከዚህ ቤት ሳሎን እስከ አረብ አገር የተዘረጋው የቤተሰባችን መረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል›› አባባ ሲናገር አዳዲስ እና ሰምቻቸው የማላውቃቸውን ቃላት እመዘግባለሁ ለምሳሌ ‹የሞት ሽረት ትግል› ‹ተርታ› ቶርታ መስሎኝ ነበር! ሃሃሃ ደግሞ እኮ አባባ ቁም ነገር የምፅፍ መስሎት ፅፌ እስክጨርስ ንግግሩ ንገታ እያደረገ ይጠብቀኛል! ቀጠለ ‹‹እንግዲህ በዚህ ትግል ውስጥ ለእድገታችን እንቅፋት የሆነብን እና ለእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ጋሬጣ እየሆነ ያስቸገረን የእናታችሁ የሽብር ድርጊት ነው›› አለ! ሽብር የሚለውን ቃል ጠበቅ አድርጎት ነበር .....አአአአአአአአአአአአአአአአአ እናታችን ሽብር ድርጊት ውስጥ ተገኘች........ ጉድፈላ! እርስ በርሳችን ተያየን ‹‹አዎ እናታችሁ በአለም አቀፍ ደረጃ በግልጥ የሽብር ድርጊት ተብለው ከተቀመጡት ወንጀሎች ያልፈፀመቻቸው የሉም ቢባል ማጋነን አይሆንም›› ታላቅ እህታችን እጇን አወጣች ‹‹እሽ ባንችአምላክ እድሉን ሰጥቸሻለሁ ›› አላት አባባ .........ኧረ አባባ ነገሩን አካበደው ‹‹አመሰግናለሁ ....የእኔ ሃሳብ አንደኛ የምንሰማው ነገር ስለእኛ እናት መሆኑን ተጠራጥረናል .....ሁለተኛ ክሱ እየቀረበባት ያለችው እናታችን ምን ስላጠፋች ነው ይሄ ሁሉ በደል የሚደፈደፍባት ›› አለች እንባ እየተናነቃት የእናታችን ነገር አይሆንላትም እማማ ስታስነጥስ ሳይቀር እህቴ አብራታ ስነጥሳለች! አረማመዷ አነጋገሯ ሁሉ እንደማማነው! ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው ....እንግዲህ ሌላ ሌላውን ትተነው ዋና ዋና የሽብር ድርጊቷን ብንመለከት 1ኛ . እናታችሁ አንድም ቀን በጎ ነገር አስባእና ተመኝታ አታውቅም ......ለምሳሌ አብረሃም እስከሁለት ሰአት ቢያመሽ ምንም እንኳ ከበለጠ ሻይ ቤት ባያልፍም ..... ልጀን መኪና ገጭቶት ነው ልጀ ሰውጋር ተጋጭቶ ታስሮ ነው ልጀ በምሬት በሱዳን በኩል አልፎ አሜሪካ ገብቶ ነው የሚሉና ሌሎችንም ጭንቀቶች በቤተሰቡ ላይ በመንዛት የሚማሩት ልጆች በጭንቀት እንዳያጠኑ እኔም ስራ ውየ መጥቸ እንዳላርፍ ትልቅ ስነልቦናዊ ስጋት ስትነዛብን ከርማለች ....በዚህም ክንያት መላ ቤተሰቡ ስጉ በርጋጊ ሁኗል›› አጀንዳውን ገለጥ ገለጥ አደረገና ‹‹ባለፈው ሰላማዊት (እህታችን ናት) አንድ ልጅ መውደዷን ተከትሎ እናታችሁ የሚያሸብር ድርጊት ስትመክራት በጆሮየ ሰምቻለሁ .... ሰው የሌሌበት ቦታ አትሂጅ ወደሰው ጅብነት የሚቀየሩ ወንዶች አሉ እየተባለ ይወራል በማለት ልጅቱ ወንዶችን ከጅቦች ጋር አቀላቅላ እንድትመለከት በማድረግ ወደፊት ለትዳር የሚኖራትን አመለካከት ሳይቀር አዛብታባታለች ድሮ ‹ሃኒየ እያለች በእንቅልፍ ልቧ የምታወራው ልጅ ይሄው ዛሬ በላኝ ነከሰኝ እያለች ሌሊቱን ስትቃዥ ነው የምታድረው›› ‹‹ዋውና አስከፊው ነገር ደግሞ የመንቀሳቀስ መብቱ ከግዜር የተቸረውን ሰውየ እናትነት ስልጣኗን ያለአግባብ በመጠቀም ማገቷ ነው ሴቶቼ ከቤት እንዳይወጡ እና ጓዳ ለጓዳ እንዲርመጠመጡ ወንዶቹም እንደ ዶሮ አስራ ሁለት ሰአት እቤታቸው ገብተው እንዲሰፍሩ አድርጋለች .....እነዚህ ልጆች ወጣ ካላሉ ሰው ጋር ካልተደባለቁ እጣ ፋንታቸው ምን ይሆናል .....አዎ የሁላችሁም ፊት የቀላው ድሎት አይደለም የፀሃይ እጥረት ነው!›› አለና ተራ በተራ ተመለከተን ....አባባ ጠቆር ስለሚል በቆዳችን ቀለም እሱን አለመምሰላችን እና ሁላችንም በእናታችን መውጣታችን ሳያበሳጨው አልቀረም ‹‹ሌላው እኔንምእራሴን የት ወጣህ የትገባህ በሚል ጥያቄ እና ፋታ በማይሰጥ ክትትል መቆሚያ መቀመጫ ማሳጣቷ አስከፊው ግፍና በደሏ ነው ....አሁን በቀደም እለት እስከ ሶስት ሰአት በማምሸቴ ጠፋ ብላ ፖሊስ ጣቢያ አስመዘገበች ሶስት ሰአት አሁን ምን አላት ....ሁላችሁም ታውቃላችሁ መቸለታ ነው ደግሞ አድማሱ (ወንድማችን ነው) ነስር ቢያነስረው ነጠላዋን አንጠልጥላ በመሮጥ ልጀን ደበደቡት ብላ አመለከተች ......እንግዲህ ይሄ ቤተሰብ ቦንብ እስኪፈነዳበት ካልጠበቀ በስተቀር ከዚህ በላይ ሽብር ምን አለ›› በማለት አብራራ! በእርግጥ እናታችን ከሚገባው በላይ የምትጨነቅና ጭንቀቷ የሚያስጨንቅ አይነት ሴት ነበረች ግን በአሸባሪነት የሚያስፈርጃት ነው ብለን አልጠበቅንም ነበር! ቀስ ብየ እጀን አወጣሁና ‹‹ እማማ ገባየ ሂዳለች እና በሌለችበት ጉዳዩን ከመመልከት እስክትመጣ ጠብቀን ማስጠንቀቂያ ብንሰጣት›› ስል እህትና ወንድሞቸ በሃሳቤ ተስማሙ አባባ ግን ተቆጣ ‹‹ምን ማለትህ ነው ......ትላንት ለዛሬ ጧት በእርሷ ዙሪያ ስብሰባ እንደሚኖር ከምሽቱ ሁለት ሰአት ከ 19 ደይቃ ላይ ነግረያታለሁ ...ሆነ ብላ ነው ዘንቢሏን ይዛ ስብሰባውን በማን አለብኝነት እረግጣ የጠፋችው...... ስለዚህ ጉዳዩን በሌለችበት ልናይ ተገደናል ደግሞስ በቁጥጥር ስር ያልዋለ አሸባሪ ከመቸ ወዲህ ነው ሊፈረድብህ ነውና ተገኝ ሲባል የሚገኘው›› ‹‹አካሄድ›› አለች ትርሲት ‹‹ገና የእናታችን ሽብርተኝነት ላይ ቤቱ ውሳኔ ሳያሳልፍ ‹አሸባሪ› ብሎ መጥራቱ ልክ አይደለም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ›› አለች ብዙሃኑ ተስማማበት ! ቢሆንም ወንድማችን ዳንኤልና እህታችን እልፍነሽ ከአባባ ጎን ወግነው ቆሙ..... ዳንኤል በእማማ ሱሰኝነቱ ስለተደረሰበት እና በፍልጥ ስላንቆራጠጠችው እማማን መደገፍ አልፈለገም... እልፍነሽም ብትሆን የምትለብሳቸው ልብሶች ላይ በእማማ የተጣለባት ከባድ ማእቀብ ስላበሳጫት እንጅ አባባ ያለው ነገር ገብቷት እንዳልሆነ የታወቀነው ቢሆንም አባባ እችን ልዩነት ተጠቀመባት እሱም ቢሆን ማታ ማታ አንድ ሁለት ብሎ መግባቱ በእማማ ተቀባይነት ስላጣ እማማን በአሸባሪነት ፈርጆ እንዳሻው ለመሆን ካለው ፅኑ ምኞት ይህን ስብሰባ እንደጠራ ግልፅ ነው! በመጨረሻም አባባ ያላልነውን ያልወሰነውን ‹ውሳኔ› ብሎ አቀረበ ‹‹ወ/ሮ ማንያህልሻል ተክሌ ......በ...... ክፍለ ከተማ በምንትስ ወረዳ የቤት ቁጥር .....ነዋሪ የሆነ ቤተሰብ ላይ ከፍተኛና የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ሲሰነዝሩ መቆየታቸው በቤተሰቡ አባወራና ቆራጥ ልጆች (ወደ ደገፉት እየተመለከተ) በተቀናጀ ክትትል ተደርሶባቸዋል በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ወ/ሮ ማን ያህልሻል ክፍሌ ‹ሽብርተኛ ተብለው እንዲፈረጁ› ቤተሰቡ ወስኗል! ከዚህ እለት ጀምሮ በልብስ ላይ በመጠጥ ላይ እንዲሁም በመግቢያና መውጫ ሰአት ላይ በእርሳቸው በኩል የሚጣሉ መአቀቦች ተቀባይነት አይኖራቸውም›› በማለት አወጀ የደገፉት አጨበጨቡለትስብሰባው በተበተነ አምሰት ደይቃ ውስጥ ሁለት እህቶቸ አጫጭር ታፋቸው ላይ የቀረ ብጣቂ ቀሚስ ለብሰው ከየምኝታ ቤታቸው ብቅ አሉ ....ዳንኤል አይኑን እያጉረጠረጠ ወደ ውጭ ሮጠ ሊያጨስ እንደሆነ ነቅቸበታለሁ ....አባባ ጠራኝና ‹‹አብረሃም ና እስቲ ከወልዴ ግሮሰሪ ሰባት ቢራ ገዝተህና አለኝ! እራሳቸው ባወጡት ህግ እንዲህ አለማቸውን መቅጨት አለ እንዴ ሆሆ! ቢራ ልገዛ መንገድ እንደጀመርኩ እናቴ ጠራራው ከንፈሯን አድርቆት በወዛደር አንድ ጆንያ ከሰል አሸክማና ዘንቢሏን በቤተሰቡ አስቤዛ ሞልታ ከገባያ ስትመለስ አገኘኋት ስታሳዝን አሁን እቤት ገብታ በአሸባሪነት ለፈረጅናት ተሰብሳቢወች ምሳ ታዘጋጃለች! በጭንቀት እየተመለከተችኝ ‹‹አቡቹ የት እየሄድክ ነው በዚህ በጠራራ እንኳን እቤት አረፍ ብትል ምናለ .....እራስህን ያምሃል ቶንሲልህም ይነሳል ምን ይሻለሃል ....ደግሞ መሃል መንገድ ላይ መኪና ድንገት ቢመጣስ ዳርዳሩን አትሄድም ......›› አለችኝ ዘንቢል ባልያዘ እጇ ራሴን እያሻሸችኝ! .....................ማሚ ከሽብር ድርጊቷ አልተቆጠበችም!!
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free