ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ከባህር የወጣች አሳ
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ከባህር የወጣች አሳ
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
=> ከዴርቶ ጋዳ የተወሰደ
=> እናታችን አሸባሪ ናት
=> የደብሪቱ ወተት
=> የመጨረሻው ኑዛዜ
=> ፍለጋ
=> ”እናቴ አልዳነችም! ...
=> ከባህር የወጣች አሳ
=> ጭለማና ብርሀን
=> ሠላማዊ ህልም
=> የዕብደት ዋዜማ
=> የአስከሬኑ ሳጥን የመጨረሻ ሚስማሮች
=> ሁለት ፅንፎች
=> ከስሜት መፋታት! Written by ደራሲ - ጁሊ በርግማን ትርጉም- ኢዮብ ካሣ
=> ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያስለቅሳል . . .
=> ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
=> love
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
ብርድ እንዳገረጣት - እንደ ወይራ ቅጠል፣ ድምፁ እንደሚሰማው፣ እንደ ክረምት ማዕበል፣ በምልምል ግንድ ላይ፣ አንድ ዘለላ ቅጠል፣ ሆኜ የአሸንቋጦ፣ ነፋስ አወዛውዞ፣ ሊጥለኝ ነው ቆርጦ፣ (ግጥም - አሌክሳንድር ፑሽኪን) - አያልነህ ሙላቱ እንደተረጎመው - ከፖቶማክ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኘው ሬስቶራንት በረንዳው ላይ ተቀምጣለች። ይህ ዋሽንግተን ዲሲ ነው። ወንዙን የተሻገረ ግን ቨርጂኒያ ገባ ማለት ይሆናል። ዓይኖቿን አሻግራ ወንዙን በዝምታ ስታጤነው ቆየች። ከመኖሪያዋ ርቃ ወደዚህ ሬስቶራንት የመጣችው ብቻዋን መሆን በመፈለጓ ነበር። ያዘዘችውን የሎሚ ጭማቂ ቀመስ አደረገችለት። እና እጇ ላይ ሲታሽ የከረመውን የቾምስኪ መጽሐፍ ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አንድ መልከቀና ጎረምሳ በቀጥታ ወደሷ ሲመጣ ተመለከተች። በፈገግታ እንደተዋጠ እጁን ዘርግቶ ሰላምታ አቀረበላት። አላወቀችውም። ቢሆንም እሷም ፈገግ ብላ የተዘረጋላትን እጅ በትህትና ጨበጠች። “አበሻ ነሽ አይደለም?” “ልክ ነው” “ብሩክ እባላለሁ” “ብርቱካን” የጨበጠውን እጇን እንደያዘ፣ “መቀመጥ እችላለሁ?” ሲል ጠየቃት። “ይቻላል” አለች እያመነታች። አስተናጋጁ ሲመጣ ብሩክ ቢራ አዘዘ። ከወፍራም ጥጥ የተሰራ ኒውዮርክ የሚል ጽሑፍ ያለበት ቤዥ ሹራብ ለብሶአል። በስፖርት የዳበረ ሰውነቱ፣ የለበሰውን ሹራብ አስጨንቆታል። በጄይል የታሹ የጠጉሩ ዘለላዎች እንደ ማረቆ ቃሪያ ጭራቸውን ጠቅልለው አናቱ ላይ ተጋድመዋል። የመካከለኛ ጣቱ ላይ ያጠለቀው የጉርጥ ዓይን የመሰለ ወፍራም ቀለበት ላይ በጥቁር ቀለም የተቀረፀው “B” የፊደል ፈርጥ ያብረቀርቃል። “አይቼሽ አላውቅም። አዲስ ነሽ?” ሲል ጠየቃት። “ልክ ነው፣ አዲስ ነኝ። አንተስ?” “ሁለት ዓመት ሆኖኛል። በሜክሲኮ በኩል በእግር ነው የገባሁት። OLF ብዬ ነበር የፖለቲካ ጥገኛነት ጥያቄ ያቀረብኩት። አሽተው፣ አሽተው በመጨረሻ ሰጡኝ። አንቺስ?” ብርቱካን ሳቀች። ከልቧ በመሳቋ ብሩክም የመዝናናት ስሜት አደረበት። በርግጥ ለምን እንደሳቀች አልገባውም። ለጠየቃት ጥያቄ መልስ አለመስጠቷንም ቢሆን ልብ አላለም። እና ወደ ሌላ ርዕስ ከመዝለቁ በፊት እሷ ቀጠለች፣ “የአዲስ አበባ ልጅ ነህ?” “እንዴታ!? የዶሮ ማነቂያ ልጅ ነኝ። በርግጥ የተወለድኩት አሜሪካን ግቢ ነው። አንቺስ?” “ፈረንሳይ” አለች። “ኦ! የፈረንሳይ ልጅ ነሻ!?” ብሩክ በጣም አዳነቀ፣ ከዚያም አልፎ አካበደ፣ “… 10ኛ ክፍል እያለሁ አንዲት የፈረንሳይ ልጅ ጠብሼ ነበር። ቁንጅናዋን ልነግርሽ አልችልም። እግሯ የሚመጠጥ ሸንኮራ። ዳሌዋ የሚገላበጥ ማዕበል። ስትስቅ ጨረቃ። ከንፈሯ አይስክሬም። ብቻ ምን አለፋሽ … አንቺን ነበር የምትመስለው … እየቀለድኩ እንዳይመስልሽ …” ብርቱካን መሳቋን በመቀጠሏ … “ማርያምን!” አለና እጇን እንደመያዝ አደረጋት። ገፅታዋን አጤነና ግን መልሶ ለቀቃት። እና ንግግሩን ቀጠለ፣ “… ገና ስገባ ሳይሽ ማርቲ ናት ትዝ ያለችኝ። ማርታ ነበር ስሟ። አባቷ ገንዘብ የተረፈው ልጥጥ ነበር። የፈለግሁትን ጠይቄያት ታሽረኝ ነበር። ገና ስገባ ሳይሽ እኮ፣ ‘ማርቲን የመሰለች ልጅ’ ብዬ ተዋወቅሁሽ እንጂ፣ ስራ ነበረኝ።” “ምንድነው የምትሰራው?” ስትል ጠየቀችው። “ታክሲ እሰራለሁ” አያያዘና ቀጠለ፣ “ስምሽን ብርቱካን ስትይኝ ወዲያው ወደ ጭንቅላቴ የመጣውን ልንገርሽ? የኔ ስም ብሩክ ነው። ያንቺ ስም ብርቱካን። የሁለታችንም ስም፣ ‘B’ በሚለው መጀመሩ አጋጣሚው አይገርምም?” ብርቱካን እንደገና በጣም ሳቀች። ብሩክም በሳቁ አጀባት። እና ወጉን ቀጠለ፣ “አግብተሽ ነው የመጣሽው?” “ማለት?” አለች ግራ ተጋብታ። “Citizen ፈርሞልሽ ነው አሜሪካ የመጣሽው?” “አይደለም …” አለች። “አግብተሽ ከሆነ የመጣሽው እንዳትወልጂለት ልመክርሽ ብዬ ነው። አዘናግተሽ ሽው ማለት ነው። አመቻችቶ፣ ‘ቻዎ!’ ማለት የተለመደ ነው። ሁሉም እንደሱ ነው የሚያደርገው። ካላገባሽ ግን ጣጣ የለውም። በይ የሆነ ነገር ጠጪ፣ እኔ ነኝ የምከፍለው …” ብርቱካን ተጨማሪ ነገር ማዘዝ ባለመፈለጓ ብሩክ ለራሱ ሌላ ቢራ አዘዘ፣ “የሚበላ ይምጣ?” “ምሳ ወስጃለሁ፣ አመሰግናለሁ።” ካለች በሁዋላ፣ ግንባሯን ቋጠር አድርጋ ጠየቀችው፣ “2005 ላይ የት ነበርክ?” ታሪኩን ባጭሩ አጫወታት። ከኢትዮጵያ ከወጣ ዘጠኝ ዓመታት አልፎታል። ስደት የጀመረው በሱዳን በኩል ነበር። ሊቢያ ገባ። የመኖሪያ ወረቀት ስላልነበረው ተያዘና ሁለት ዓመታት ታሰረ። ጊዜውን ጨርሶ ሲፈታ ወደ ኬንያ አቀና። በመቀጠል በኡጋንዳ በኩል፣ ብሩንዲን በማቋረጥ በማላዊ ሐይቅ ላይ በጀልባ ተጉዞ፣ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ተሻገረ። ደቡብ አፍሪቃ ላይ ብዙ ስቃይ ገጥሞት ነበር። ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ፣ ከቻይና ነጋዴዎች ጋር ጥሩ ቢዝነስ ሰራ። ደህና ገንዘብ ከያዘ በኋላ አስር ሺህ ዶላር ከፍሎ ሜክሲኮ ደረሰ። ከሜክሲኮ በእግር ጉዞ ድንበር ሰብሮ አሜሪካ ገባ። አሁን ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ታክሲ ነጂ ሆኖአል። የዘጠኝ ዓመታት የጉዞ ታሪኩን እንዲህ ቀለል አድርጎ ነገራት። ታሪኩን ተርኮ ሲያበቃ የብርቱካንን ገፅታ መጨላለም እንኳ ሳያስተውል ወደ ሌላ ጥያቄ ተሸጋገረ፣ “እስኪ ያንቺን ታሪክ ንገሪኝ?” ሲል ጠየቃት። “እንዳንተ የሚነገር ታሪክ እንኳ የለኝም” አያያዘችና ቀጠለች፣ “… ትንሽ ሴት ልጅ አለችኝ። ሐሌ ትባላለች …” “ዋው!” አለ በአድናቆት፣ “… ፎቶዋ አለሽ?” ከቦርሳዋ አወጣችና አሳየችው። ብሩክ በተመስጦ ካስተዋላት በኋላ፣ “ቆንጆ ልጅ አለችሽ” አለ። በመቀጠል የጠየቃት ጥያቄ ብርቱካን ይጠይቀኛል ብላ የጠበቀችውን አልነበረም። “አዲስ አበባ ምን ትሰሪ ነበር?” ሲል ጀመረ፣ እንደማሰብ ካለች በኋላ፣ “የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ እሰራ ነበር” ስትል መለሰች። “ስራሽን ትተሽ ነው አሜሪካ የመጣሽው?” “አይደለም። ታስሬ ነበር …” “ታስረሽ ነበር?” በመደነቅ ጠየቃት። የብሩክን የመገረም ምክንያት ለማወቅ ብርቱካን በጣም ጓጓች። ብሩክ፣ “እኔም አዲስ አበባ ታስሬ ነበር” ካለ በኋላ ማብራራቱን ቀጠለ፣ “… በሚገርም ሁኔታ የኔና ያንቺ ታሪክ ተመሳሳይ ነው። እኔንም አስረው አሽተውኛል። ታደሰ የተባለ መርማሪ ወያኔ ነው የተጫወተብኝ። እንዴት ገልብጠው እንደገረፉኝ … በኋላ ጀርባዬን አሳይሻለሁ።” ብሩክ እንደገና እጇን ለመያዝ እየሞከረ፣ “ዛሬ ከኔ ጋር ነሽ አይደለም? የራሴ ክፍል አለኝ። አንድ ደባል ብቻ ነው ያለኝ። ሌሊት ስለሚሰራ ብቻችንን ነው የምንሆነው …” እያለ ተለማመጣት። ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ እጇን በዝግታ ካስለቀቀችው በኋላ ጥያቄ ጠየቀችው፣ “የት ነበር የታሰርከው?” “6ኛ። አንቺስ?” “እኔ ቃሊቲ ነበርኩ። ለምን ነበር ያሰሩህ?” “የገንዘብ ጉዳይ ነው። ልጥጦች ጋር እሰራ ነበር። አዘናግቼ ደህና ፍሉስ ከነትኳቸው። ምን ያደርጋል፣ ከተያዝኩ በኋላ ጉቦ ከፍለው አስቀጠቀጡኝ። ቢሆንም ግን አላመንኩላቸውም። ምንም ማስረጃ አልነበራቸውም። በመጨረሻ ዳኛው በነፃ ለቀቀኝ።” በጣም ሲስቅ ቆየና እንዲህ ሲል ጠየቃት፣ “አንቺስ ለምን ታሰርሽ?” “የፖለቲካ ጉዳይ ነው …” “ፖለቲካ!? ፖለቲከኛ ነሽ እንዴ? እኔኮ ጮካ መስለሽኝ ነበር።” እንደገና እጇን ሊይዝ ሞከረና መልሶ ተወው። መጠየቁን ግን አልተወም፣ “አንቺ ግን ለምን ፖለቲካ ውስጥ ገባሽ?” “ስለ ቅንጅት ሰምተህ ነበር?” ስትል ጠየቀችው። “ቅንጅት?” አለ ነቃ ብሎ፣ “… ስለ ቅንጅት እማ በደንብ አውቃለሁ።” ቅንድቡን ወደላይ ዘርግቶ ቀጠለ፣ “… ልደቱ የሚባል ሰው ከእናንተ ጋር ነበረ አይደለም?” ሲል ጠየቃት። እየሳቀች፣ “ልክ ነህ” አለችው። በእርግጠኛነት እና በስሜት ማብራራቱን ቀጠለ፣ “… ወያኔዎቹ ለልደቱ አንዲት ንቅሳታም ትግሬ አጣብሰውት ከዳቸው ሲባል ሰምቻለሁ። እናንተ ግን ሸዋዬ ነገር ናችሁ። እንዴት ነቄ መሆን አቃታችሁ? ግን ልጠይቅሽ እስኪ አሁን ቅንጅት የት ነው ያለው?” ብርቱካን ከዚያ በላይ ከብሩክ ጋር መቆየት እንደማትችል አወቀች። በዚያችው ቅፅበት በድንገት ገፅታዋ የተለበለበ ግንድ መምሰሉንም ቢሆን ብሩክ አላስተዋለም። በድንገት ለምን እንዲህ እንደተለወጠች መረዳትም አልቻለም። እና ብሩክ ግራ ተጋባ። ለመሄድ መፈለጓን በመግለፅ ስትሰናበተው ብሩክ፣ “ለመሄድ ከፈለገች ምን ይደረጋል?” በሚል እሱም ተሰናበታት። በርግጥ ለምናልባቱ በሚል የስልክ ቁጥሩ የተፃፈበት ካርዱን አስይዟታል። እንድትደውልለትም ተማፅኖአታል። ብርቱካን ከሬስቶራንቱ ወጣች። የዋሽንግተን ዲሲ ተስያት ጭጋጋማ ነበር። ጉሙ እስከ ወንዙ ወርዶአል። በእርጋታ በእግሯ አዘገመች። በድንገት አየሩ ተለወጠ። ለሆሳስ የነበረው ንፋስ ማፉዋጨት ያዘ። ጭጋጉን ይበታትነው ጀመር። በርግጥ ረጅም ርቀት ማየት የሚቻል አልነበረም። ለቨርጂኒያ ጀርባዋን ሰጥታ መንገዷን ቀጠለች። ለአፍታ አሜሪካ ላይ፣ “ግማሽ ሚሊዮን ይደርሳል” ስለሚባለው አበሻ አሰበች። “ስንቶች ይሆኑ እንደ ብሩክ?” የሚል ጥያቄ አዕምሮዋን አቋርጦ አለፈ። ሳታስበው፣ “አምላኬ” የሚል ቃል ካንደበቷ አፈትልኮ ወጣ። በለሆሳስ መፀለይ ፈልጋ ነበር። አልቻለችም። እንደ መብረቅ የተወረወረ ሽምጥ ነፋስ፣ ቃሉን ከከንፈሮቿ ላይ መንጭቆ ወሰደባት። ፍርሃት እና ብርድ ተቀላቅለው አንጀቷ ውስጥ የገቡ ያህል ውስጧ ቀዘቀዘ። እና ብርድ እንደበረታባት እርግብ ኩምትር አለች። ፖቶማክ ወንዝ ሲጓዝ ከጀርባ ሰማችው። እንደ ቢጫ ቅጠል አንስቶ ወንዙ ላይ ሊጨምራት እልህ ከተጋባው ነፋስ ጋር እየታገለች ወደፊት አዘገመች። የለም! የለም! ወደፊት አዘገመች ማለት እንኳ ይቸግራል። ነፋሱ ክፉኛ ወደኋላ እየገፋት ነበር … ተስፋዬ ገብረአብ (አጭር ልቦለድ ድርሰት - ነኀሴ፣ 2012)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free