ማይክሮሶፍት አዲሱን
ዊንዶው 10 ኦፕሬቲንግ
ሲስተም በሚቀጥለው
ሀምሌ ወር እንደሚለቅ አስታወቀ። ማይክሮሶፍት
በፈረንጆቹ ሀምሌ 29
ለገበያ የሚያቀርበው
ዊንዶው 10 ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ከዚህ ቀደም
የነበሩትን ዊንዶው 7 እና 8 በቀላሉ በማሳደገ
ወይም አፕግሬድ
በማድረግ ልንጠቀምበት
እንደምንችል ነው
ያስታወቀው። ዊንዶው 10
ለኮምፒውተሮች እና
ታብሌቶች የተመቹና
አዳዲስ ገጽታዎችን ይዞ
መቅረቡንም ኮርፖሬሽኑ
ትናንት በሰጠው መግለጫ አመላክቷል። አዲሱ ዊንዶው 10
ለሞባይል ተጠቃሚዎች
“'Edge” የተሰኘ
ኢንተርኔት መፈለጊያ
ብሮውዘር ያካተተ
መሆኑም ተገልጿል። ዊንዶው 7 እና 8.1
ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን
በቀላሉ እና ያለምንም
ክፍያ ወደ ዊንዶው 10
ማሳደግ እንደሚቻልም
ነው ማይክሮሶፍት ያስታወቀው። ማይክሮሶፍት ከዚህም
በተጨማሪ ዊንዶው 10
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
የሚጠቀሙ አዳዲስ
ኮምፒውተሮችና
ስልኮች ከመጪው ወር ጀምሮ ለገበያ
እንደሚያቀርብ
ጠቁሟል። በያዝነው የፈረንጆቹ
አመትም ስማርት
ስልኮች ዊንዶው 10
እንዲጠቀሙ ለማድረግ
እየሰራ መሆኑን
መግለጹን ሬውተርስ ዘግቧል።
|