የስልኮት ባትሪ በፍጥነት
እያለቀ አስቸግሮታል?
እንግዲያውስ
የሚከተሉትን አማራጮችን ስክሎት
ላይ በማስተካከል
የባትሪዎትን ህይወት
ማርዘም ይችላሉ፡፡ 1 ለወራት
ያልተቀሙባቸውን
አፕሊኬሽኖች ወይም
መተግበሪያዎች
ማጥፋት ስልኮት ላይ ጭነዋቸው
ነገር ግን ለወራት ምንም
ጥቅም ላይ ሳያውሏች
ግን ኢንተርኔት
በሚጠቀሙበት ጊዜ
ኖቲፊኬሽን እና የመሳሰሉትን የሚልኩ
አፕሊኬሽኖች
የባትሪዎትን ህይወት
ሊያሳጥሩት ይችላሉ፡፡ ስለዚህም እነኚህን
አፕሊኬሽኖች ከስልኮት
ላይ ማጥፋት
የባትሪዎትን ህይወት
ከማራዘም ባለፈ
ከአላስፈላጊ የኢንተርኔት ወጪ ሊያድኖት
ይችላል፡፡ 2 ጠቃሚ ያለሆኑ
አፕሊኬሽኖች
Background data
እንዳይጠቀሙ
ማድረግ ኢንተርኔት
በሚጠቀሙበት ጊዜ
Background data
የሚጠቀሙ
አፕሊኬሽኖችን ሴቲንግ
ውስጥ በመግባት Background data
እንዳይጠቀሙ
በማድረግ የባትሪዎትን
ህይወት ማራዘም
ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ብዙ ጊዜ
የማይጠቀሙባቸውን
አፕሊኬሽኖችን ወይም
መተግበሪያዎች
በመምረጥ
Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ
ይችላሉ፡፡ 3 በተደጋጋሚ
አፕሊኬሽኖችን
ከመዝጋትና መክፈት
መቆጠብ ብዙ ጊዜ እንደነ ኦፔራ
ሚኒ፣ፌስ ቢክ የመሳሰሉ
አፕሊኬሽኖችን
ተጠቅመን ስንጨርስ
ዘግተን ከጥቂት
ደቂቃዎች በኋላ መልሰን እንከፍታለን፡፡ ይህን ተግባር
በተደጋጋሚ ባደረግን
ቁጥር ለሞባይላችን
ባትሪ ጠንቅ እንደሆነ
ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህም ከተጠቀምን
በኋላ የሆም በተኑን
ተጠቅመን በመውጣት
ሌላ ጊዜ መጠቀም
ስንፈልግ ሞባይላችን
ካቆመበት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ
የሞባይላችንን ባትሪ
እድሜ እንዲኖረው
ያደርገዋል፡፡ 4 የስልኮትን
ቫይብሬሽን ማጥፋት ስልክን በሪንግቶን ብቻ
መጠቀም ለብዙዎቻችን
አስቸጋሪ እንደሚሆን
ግልፅ ነው ሆኖም ግን
የባትሪዎትን ህይወት
ማስረዘም ሀሳብ ካለዎት ግን የስልኮን ቫይብሬሽን
ማጥፋት ጠቃሚ ሊሆን
ይችላል፡፡ ይህንንም ለማድረግ
የስልኮት የድምፅ
አማራጭ ላይ በመግባት
የቫይብሬሽን አማራጭ
ማጥፋት፡፡ 5 የስልኮን ብሉቱዝ
አማራጭ ማጥፋቶን
ማረጋገጥ አብዛኛዎቻችን
ምንፈልገውን ነገር
ከወዳጆቻችን ጋር
ብሉቱዝን በመጠቀም
ከተላላክን በኋላ
ብሉቱዛችንን ማጥፋት እንዘነጋለን ይህ ደግሞ
ለባትሪያችን ህይወት
ማጠር እንደ ምክንያት
ይነሳል፡፡ ለዚህም
እንደአማራጭነት
የቀረበው ሁልጊዜ
ብሉቱዛችን መጥፋቱን
ማረጋገጥ እንዲሁም
ከሰዎች ጋር ዳታን ከተላላክን በኋላ
ወዲያውኑ ማጥፋትን
አለመዘንጋት ነው፡፡ ምንጭ፡ ታይም መፅሄት
|