ሰሞኑን በፌስቡክ
ወሲባዊ ይዘት ያላቸው
ተንቀሳቃሽ ምስሎች እኛ
በማናውቀው መንገድ በስማችን ጓደኞቻችን
ታግ እየተደረጉ ነው። ታግ የተደረግነውን
ምስል ስንጫነውም
ሌሎች ጓደኞቻችን እኛ
በማናውቀው መንገድ
ታግ እያደረግናቸው
የሳምንቱ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። ዘደብሪፍ የተሰኘ ድረ
ገጽ በዘገበው ለዚህ ሁሉ
ችግር ትሮጃን
የተባለውን ቫይረስ
በምክንያነት
አስቀምጦታል። እስካሁንም ከ100 ሺህ
በላይ የፌስቡክ
ተጠቃሚዎች በዚሁ
ቫይረስ መጠቃታቸውን
ነው ድረ ገጹ
ያመላከተው። ታግ የተደረገው ምስል
ወይም ቪዲዮ
በተጠቂው ጓደኛ
ጓደኞች ሊታይ
መቻሉም በቫይረሱ
የሚጠቁትን ሰዎች ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል
ተብሏል። ቪዲዮውን ከመመልከት
በፊት ተጠቃሚዎች
ተጨማሪ ሶፍትዌር
ዳውሎድ እንዲያደርጉ
ይጠየቃሉ፤ በዚህም ጊዜ
ነው ትሮጃን ኮምፒውተር የሚያጠቃ
ቫይረስ የሚለቀው ነው
ያለው ዘገባው። ስለሆነም ታግ
የተደረግነውን ቪዲዮ
ከመክፈት እና
እንድናወርድ የሚያዘንን
ነገር ከመጫን መታቀብ
ይኖርብናል። ከዚህ በተጨማሪ ታግ
የተደረግነውን ቪዲዮ
“untag” በማድረግ
ራሳችን እና ጓደኞቻችን
ከዚህ ያልተገባ ተግባር
እናድናለን ማለት ነው። እነዚህን ሁለት ነገሮች
ተግባራዊ ስናደርግ
ቫይረሱ እየጠፋ
ስለሚሄድ
በጓደኞቻችንን ገጽ
ላይም እንዳይታይ ማድረግ እንችላለን። በዋናነት ግን እንደዚህ
አይነት ስብእናችንን
የማይወክሉና
አቋማችንን
የማያመላክቱ ፎቶ
ግራፎችንም ሆነ ቪዲዮዎች ታግ
ከመደረግ ለመዳን
ሴቲንግ ውስጥ
በመግባት አልያም
www.facebook.com/
setting የሚለውን
ሊንክ በመከተል
Timeline and Tagging
ውስጥ በገጻችን ላይ ለመለጠፍ የሚሰጠንን
አማራጭ “እኔ ብቻ”
የሚለውንና ጓደኞቻችን
ታግ የሚያደርጉን ነገር
ከገጻችን ላይ
ከመውጣቱ በፊት እኛ እንድናየው መፍቀድ
ያስፈልጋል። ምንጭ፦
www.thedebrief.co.uk
|