የተሰረቀ
ስልካችን
ማንም
እንዳይጠቀምበት
ማድረግ
እንደምንችል ያውቃሉ? አንዳንድ ጊዜ በጣም
አጣዳፊ ነገር ሲገጥመን
በአቅራቢያችን
የምናገኘውን ተጠቅመን
ከችግር ለመውጣት
እንጥራለን። በዚህ ወቅትም ሞባይላችን
ተተኪ የሌለው ነብስ አድን
መሆኑ ይነገራል። ሞባይላችንን ከተመለደው
አገልግሎቱ ባሻገር
አብዛኞቻችን
የማናስተውላቸውን እና
በሞባይሎቻችን
የምናደርጋቸውን አራት ነገሮች እንመልከት። 1. ለአስቸኳይ ጊዜ
(Emergency) በአለማቀፍ ደረጃ
የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ
ለማድረግ የምንጠቀምበት
ቁጥር 112 ነው። ኔትወርክ በሌለበት አካባቢ
ወደ 112 ስንደውል
በአቅራቢያችን ኔትወርክ
በመፈለግ ለአስቸኳይ ጊዜ
እርዳታ የሚያገለግሉንን
ስልክ ቁጥሮች እንድናገኝ እንደሚረዳን ነው
የሚነገረው። ስልካችን የተቆለፈ
ቢሆንም እንኳን
የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ
ማድረግ እንችላለን። 2. የባትሪ ሃይል
ለመጨመር የሞባይላችን ባትሪ
በሚያልቅበት ወቅት
*3370# ብለን ስንጫን
ሞባይላችን ጠፍቶ
በመብራት የባትሪያችን
ሃይል በ50 በመቶ እድገት ያሳያል። ይህም የሚሆነው
ሞባይላችን
ከሚያስቀምጠው
መጠባበቂያ ሃይል ላይ
ቀንሶ ቻርጅ
ስለሚያደርገው ነው። ሞባይላችን ይህን
መጠባበቂያ ሃይልም
በቀጣይ ጊዜ ቻርጅ ስናደር
የሚጠራቀም ይሆናል። 3. የተቆለፉ መኪናዎችን
ለመክፈት በአላርም ወይም በሪሞት
ቁልፎች የሚከፈቱ
ተሽከርካሪዎችንም
ሞባይላችንን በመጠቀም
መክፈት እንችላለን። ለምሳሌ የሪሞት/
ኤሌክትሮኒክ ቁልፋችንን
ከቤታችን ረስተን ብንወጣ
እና የተለመደው ሰክተን
የምንከፍትበት የብረት
ቁልፋችንንም መኪናችን ውስጥ ብንረሳ ቁልፉ
ከቤት እስኪመጣ
ለእንግልት አንዳረግም። የሚጠበቅብን አንድ ነገር
ብቻ ነው፤ ቤት ውስጥ
ወይም ሪሞት ቁልፉ
በሚገኝበት አካባቢ
ወደሚገኝ ሰው መደወል።
ከዚያም የተደወለለት ሰው በሪሞት ቁልፉ ላይ
ያለውን “unblock” የሚል
ቁልፍ ወደ ማነጋገሪያው
ጠጋ አድርጎ እንዲጫን
ማድረግ ነው። በዚህም በተሽከርካሪው
አቅራቢያ የሚገኘው ሰው
በቀላሉ መኪናውን
መክፈት እንደሚችል
ተረጋግጧል። 4. የተሰረቀ ስልካችንን
ከጥቅም ውጪ ለማድረግ የሞባይል ስልካችን
ሴሪያል ቁጥር ለማወቅ
*#06# ስንጫን 15 ዲጂት
ያለው ቁጥር እናገኛለን። ይህም ቁጥር ልዩ እና የኛ
ብቻ በመሆኑ መዝግበን
ይዘን በጥንቃቄ ማስቀመጥ
ይኖርብናል። አይበለውና ስልካችን
ሲሰረቅ ግን ከኛ
የሚጠበቀው ይህን ባለ 15
ዲጂት ቁጥር ለአገልግሎት
አቅራቢው ድርጅት
(ለሳምሰንግ፣ ኖኪያ፣ አፕል ወዘተ..) በመወደል
ቁጥሩን መንገር ብቻ ነው
የሚጠበቅብን። የሰረቀን ሰው ሲም ካርድ
ቢቀይርም እንኳን
ሞባይሉ ከጥቅም ውጭ
ነው የሚሆነው። ምንም እንኳን
የተሰረቀብንን ሞባይል
ማስመለስ ባንችልም
የሰረቀው አካል
እንዳይጠቀምበት ማድረግ
መቻላችንም አንድ ነገር ነው። ሁሉም የተሰረቀ አካል
ይህን ተግባር ቢቀጥልበት
ሞባይል መስረቅ ከንቱ
ይሆን ነበር ይላል የአይዲያ
ዳይጄሰት ዘገባ።
|