ቢትቶሬንት ኩባንያ
በሊፕ /Bleep,/ የተሰኘ
አዲስ የጽሁፍ መልእክት
መላላኪያ መተግበሪያ/ application ትናንት
ይፋ አደርጓል። ይህ መተግበሪያ/
application የአንዲሮይድ፣
የማክ እና አይ. ኦ. ኤስ
እንዲሁም የዊንዶው
ስልኮች ላይ የሚሰራ
መሆኑም ተነግሯል። በሊፕ መተግበሪያ/
applicationን ከሌሎች
የጽሁፍ መላኪያ
መተግበሪያ ለየት
የሚያደርገውም
ተጠቃሚዎች በቅጽል ስማቸው ብቻ
በመጠቀም ከሚፈልጉት
ሰዎች ጋር መልዕክት
ለመለዋወጥ በማስቻሉ
ነው። ይህንን
መተግበሪያ ለመጠቀምም
ብሊፕ ላይ ቅጽል ስምን
በማስገባት ብቻ
ተመዝግበን መጠቀም
እንችላለን። መተግበሪያው ከሌሎች
የማህበራዊ ድረ ገጾች
ጋር ማለትም እንደ
ፌስቡክ ወይም
ኢሜይል
አገልግሎት ሰጪ ገፆች ጋር የማይገናኝ በመሆኑም
ከምንፈልጋቸው ሰዎች
ጋር ብቻ መልእክት
ለመላላክ ያስችለናል
ተብሏል። ምንጭ፦
huffingtonpost.com
|