ቶሪየም የተባለ
የኬሚካል ንጥረ ነገርን
በመጠቀም ያለነዳጅ
ለ100 ዓመት የምትነዳ ተሽከርካሪ ተፈበረከች። ተሽከርካሪዋ ቶሪየም
የተባለ የሬዲዮ አክቲቭ
ሆነ ኬሚካል ንጥረነገር
በመጠቀም
የምትንቀሳቀስ ሲሆን፥
በ8 ግራም ቶሪየም ነው ለ100 ዓመታት
የምትሽከረከረው
ተብሏል። ቶሪየም የኬሚካል
ምልክቱም "Th" ሲሆን፥
አቶሚክ ቁጥሩ 90
የሆነና በብረትነት
የሚመደብ ንጥረ ነገር
ነው። ቶሪየም በአሁኑ ወቅት
በዓለማችን ላይ በብዛት
የሚገኝ ንጥረ ነገር
ሲሆን፥ ትንሽ የቶሪየም
መጠንም ከ20 ሚሊየን
የከሰል ድንጋይ ሀይል ጋር እኩል ነው
ተብሏል። ተሽከርካሪዋን
ያመረተው ኩባንያ
እንዳስታወቀዉ
ቶሪየምን ለሀይል
ምንጭነት ለመጠቀም
ስናስብ ተሽከርካሪዎችን እንዳማራጭ ተጠቀምን
እንጂ በአመዛኝ
ትኩረታችን
ለኤሌክትርክ ሀይል
ማመንጫነት እንዲውል
ነው። ምክንያቱም በአሁኑ
ወቅት ያሉ የተሽከርካሪ
አምራች ኩባንያዎች
ፍላጎት ቶሪየምን
የሚጠቀሙ
ተሽከርካሪዎችን ከማምረት ይልቅ በነዳጅ
የሚሰሩት ማምረት
በመምረጣቸው ነው። ይሁን እንጂ ወደ ፊት
ማለትም ቢበዛ ከ10
ዓመታት በኋላ በቶሪየም
የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች
በስፋት ወደ ገበያ
መግባታቸው የማይቀር ነው ተብሏል። ቶሪየም ራዲዮአክቲቭ
በመሆኑ ምክንያት
በሰው ላይ ጉዳት
ያደርሳል የሚለው ስጋት
አይፈጥርም ሲሉም
ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። ምንጭ፦
jewsnews.co.il
|