ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - አለርጂን የሚከላከሉ የምግብ አይነቶች
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - አለርጂን የሚከላከሉ የምግብ አይነቶች
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
=> የሳንባ ነቀርሳ በሽታ
=> የውጥረት መንስኤዎችና ምልክቶች
=> ማር እና ሎሚን ቀላቅሎ መጠቀም ለጤና፣ ለቆዳ ውበት እና ለጸጉር ያለው ጠ
=> የሆድ ድርቀትን በቀላሉ መካላከል
=> የማየት አቅማችንን የሚጎዱ 10 መጥፎ ልማዶች
=> አለርጂን የሚከላከሉ የምግብ አይነቶች
=> እንቅልፍ ለመርሳት ችግር እንዳንጋለጥ ይረዳል
=> መጥፎ ስሜቶችን ለመቆጣጠር - የእጅ ጣቶቻችን ተጭነን መያዝ
=> ከእርግዝና በፊት መቋረጥ ያለባቸው 5 ጎጂ ልማዶች
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
አለርጂ ሰውነታችን እንደ ምግብ፣ ውሃ፣ አየር ወይም መድሃኒት አይነት ነገሮች ሳይስማሙት ሲቀር የሚከሰት ህመም ነው። የተለያዩ አይነት አለርጂዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥም የመተንፈሻ አካላት አለርጂ፣ የቆዳ አለርጂ፣ ከምግብ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የምግብ አለርጂ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። እነዚህን የአለርጂ አይነቶች በቀላሉ የምናገኛቸውን የምግብ አይነቶች በእለት ተእለት አመጋገባቸን ውስጥ በማካተት እራሳችንን ከአለርጂ መከላከል እንደምንችል በተለያዩ ጊዜ የተሰሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ። እነዚህ የምግብ አይነቶችም፦ ነጭ ሽንኩርት ፦ ነጭ ሽንኩርት አለርጂን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ስላለው በየእለት ምግባችን ውሰጥ ቀላቅለን መጠቀም ይመከራል። በተጨማሪም ነጭ ሽንኩርት በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ስላሉት በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ ቀላቅለን መመገብ ይመከራል። ሎሚ፦ ሎሚ በቪታሚን ሲ የበለጸገ በመሆኑ ለአለርጂ እንዳንጋለጥ የሚረዳን ሲሆን፥ እንዲሁም የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም እንዲጨምር ስለሚረዳን አዘውትረን መጠቀም ይመከራል። ስለዚህም በምንጠጣው ውሃ ወስጥ ሎሚ ጨምቀን በመጠጣት ለአለርጂ እንዳንጋለጥ ይረዳናል ተብሏል። አፕል/ፖም/ ፦ አፕል በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። አፕል በውስጡ "ኩዌርሰቲን" የሚባል ኬሚካል ስላለውም ሰውነታችን ለአለርጂ እንዳይጋለጥ ይረዳናል ተብሏል። ይህ ብቻ ሳይሆን አፕል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም ስለሚጨምር በምግባችን ውስጥ አዘውትረን መጠቀም ይመከራል። እርድ፦ እርድ በውስጡ ባለው "ኩኩሚን" የተባለ ንጥረ ነገር አማካኝነት ለአለርጂ እንዳንጋለጥ ይረዳናል። አንድ የሻይ ማንኪያ እርድ በአንድ ብርጭቆ ወተት ውስጥ በመጨመር አዋህዶ መጠጣት ይመከራል። ስኳር ድንች ፦ ስኳር ድንች እንደ "ቤታ ካሮቲን"፣ "ፖታሲየም"፣ "ማግኒዚየም" እና "ቪታሚን B6" ባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ በመሆኑ አለርጂን በቀላሉ ለመከላከል ያስችላል። ሰለዚህም የተቀቀለ ስኳር ድንችን አዘውትሮ በመመገብ አለርጂን መከላከል እንደሚቻልም ተነግሯል። ዝንጅበል ፦ ዝንጅብል አለርጂን ለመከላከል እጅጉን ይረዳል ተብሏል። ስለዚህም በቀን ውስጥ ሁለት ብርጭቆ ዝንጅብል በመጠጣት አለርጂን ለመከላከል የሚያስችለን ሲሆን፥ በተለይም ከመተንፈሻ አካል ጋር ተያይዞ የሚከሰት አለርጂን በቀላሉ ለማከም ያስችላል ተብሏል። ምንጭ፦ trendingpost.net
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free