የሆድ
ድርቀት በርካታ ሰዎችን
ሲያጋጥም ይስተዋላል። ለዚህ ህመም የሚጋለጡ
ሰዎችን ወደ ወጸዳጃ
ቤት ሄደው
በሚጸዳዱበት ወቅት
በጣም ሲቸገሩም
ይስተዋላል። ችግሩን ለመከላከል
ይረዳን ዘንድም በቀላሉ
በምናገኛቸው ነገሮች
እራሳችንን መርዳት
እንችላለን። ሎሚ፦ ሎሚ በውስጡ ባለው የሲትሪክ አሲድ
አማካኝነት የምግብ
መፈጨት ስርዓታችን
የተስተካከለ እንዲሆን
ይረዳል። ስለዚህም ሎሚን
አዘውትሮ መበጠቀም
ከሆድ ድርቀት ጋር
ተያይዞ የሚከሰቱ
ችግሮችን መከላከል
ይቻለል። በፋይበር የበለጸጉ
ምግቦች፦ በፋይበር የበለጸጉ መግቦች የሆድ
ድርቀትን ለመከላከል
እንደሚረዱም
ተጠቁሟል። ስለዚህም እንደ አጃ፣
ሩዝ፣ ገብስ፣ በቆሎ እና
ሌሎች በፋይበር
የበለጸጉ ምግቦችን
በእለት ተእለት
ምግባችን ውስጥ አዘውትሮ መውሰድ
ይመከራል። ካፌይን ፦ እንደ ቡና አይነት ያሉ የካፌይን
ንጥረ ነገሮች ያላቸውን
አዘውትሮ መውሰድም
ከሆድ ደርቀት
ለመገላገል ይመከራል። ዘይት፦ ዘይት ወይም ቅባትነት ያላቸው
ምግቦችም እንደ ሰገራ
ያሉ ነገሮች በቀላሉ
እንዲዘዋወሩ በማድረግ
የሆድ ድርቀትን
ለመከላከል ይረዳሉ። ስለዚህም ዘይትነት
ያላቸውን ምግቦች እና
ዘይት በምግባችን ውስጥ
በዛ አድርገን በመጠቀም
የሆድ ድረቀትን
መከላከል እንችላለን። ምንጭ፦
healthdigezt.com
|