በቂ
እንቅልፍ መተኛት
ለአእምሯችን ጤንነት
እጅጉን ጠቃሚ እና
እንደ አልዛይመር አይነት ላሉ የመርሳት ችግሮች
እንዳንጋለጥ
እንደሚረዳን
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ
የተደረገ ጥናት
ይጠቁማል። ከዚህ ቀደም እንደ
አልዛይመር አይነት
የመርሳት በሽታ
ያለባቸው ሰዎች
ለእንቅልፍ እጦት
እንደሚጋለጡ ይነገራል። አሁን ላይ ግን
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ
የተደረገ ጥናት
እንደሚጠቁመው
በተለይም እድሜታቸው
የገፋ ሰዎች አነስተኛ እንቅል በተኙ ቁጥር
ለበሽታው የመጋለጥ
እድላቸው የሰፋ ነው
ይለናል። ጥናቱ የተካሄደው ረዘም
ላለ ጊዜ በደንብ
እንቅልፍ ወስዷቸው
የሚተኙ ሰዎች እና
አይናቸውን ከመጨፈን
ያልዘለለ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች መካከል
ሲሆን፥ በደንብ
የማይተኙ ሰዎች
የማስታወስ ችሎታቸው
ዝቅተኛ እና ለከፍተኛ
የመስራት ችግር ወይም አልዛይመር የመጋለጥ
እድላቸው ከፍተኛ ሆኖ
ተገኝቷል። ጥናቱ ላይ
እንደተገለጸው በቂ
እንቅልፍ በምንተኛበት
ጊዜ አእምሯችን ውስጥ
የሚገኙ እና ለመርሳት
ችግር መንስኤ ናቸው የሚባሉትን መርዛማ
ፕሮቲኖች የሚከላከል
ሲሆን፥ በተጨማሪም
በቂ እንቅልፍ መተኛት
የአእምሯችንን ሴሎች
ከጉዳት የከላከላልም ተብሏል። በቂ እንቅልፍ መተኛት
ለሰው ልጅ ከእረፍትነት
በዘለለ ለአእምሯቸው
ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ
እና እንደ አልዛይመር
አይነት ላሉ የመርሳት ችግሮች እንዳንጋለጥ
ይረዳናልም ተብሏል። ስለዚህም በቂ እንቅልፍ
በመተኛት በርካታ
የጤና ተቀሜታዎችን
ማግኘት እንደምንችልም
ተመራማሪዎች
ተናግረዋል። ምንጭ፦
huffingtonpost.com
|