የውጥረት መንስኤዎችና ምልክቶች – Stress ውጥረት ሰውነታችን በተለያዩ ሁኔታዎች
ውስጥ ለምሳሌ በአደጋ ጊዜ በሕመም ወቅት
የሚያሳየው መደበኛ የሆነ ሪአክሽን ወይንም
ምላሽ ነው :: ለምሳሌ አደጋ በሚያጋጥመን
ጊዜ ሰውነታችን ከአደጋው ለማምለጥ
እራሱን ያዘጋጃል :: ውጥረት ሰውነታችን እራሱን ከአደጋ የሚታደግበት መንገድ ነው
:: በትክክለኛው መጠን በሚሰራበት ጊዜ
ወጥረት ሂዎት አድን የሆነ የተፈጥሮ
ክስተት ነው :: እንደዚሁም መደበኛ
ውጥረት ኃይልና ጉልበት ሆኖ የዕለት
ተለት ስራችንን እንድናከናውን የሚረዳን ነው ለምሳሌ ፈተና ሲኖርብን ትንሽ ስትረስ
ሲሰማን በርተትን እንድናጠና ይረዳናል ::
ስትረስ ከመደበኛ መጠኑ ሲያልፍ ግን
ጠቃሚ መሆኑ ይቀርና ኑሮአችንን
የሚያውክ ይሆናል :: ውጥረት እንዴት ይፈጠራል አንዳች አስደንጋጭ ነገር በሚገጥመን ጊዜ
የነርቨስ ሲስተማችን የተለያዩ የስትረስ
ሆርሞኖችን ያመነጫል :: ከነዚህ መካከል
በዋናነት የሚጠቀሱት አድሬናሊን እና
ኮርቲዞል ናቸው :: እነዚህ ሆርሞኖች
ሰውነት ከአደጋው ለማምለጥ እንዲዘጋጅ ይረዱታል :: ልብ በጣም መምታት
ይጀምራል ጡንቻዎች ይኮማተራሉ የደም
ግፊት ይጨምራል ትንፋሽ ይፈጥናል በዚህ
መልኩ ሰውነት ከአደጋ ለማምለጥ ዝግጁ
ይሆናል :: የውጥረት ምልክቶች የውጥረት ምልክቶች በአራት ይከፈላሉ የአስተሳሰብ ምልክቶች የመርሳት ችግር ፎከስ ማድረግ አለመቻል ትክክለኛ ያልሆነ ውሳኔ አሉታዊ ነገሮችን ብቻ ማሰብ እጅግ ፈጣን የሆነ ማሰብ ሁልጊዜ መስጋት የስሜት ምልክቶች ስሜት ቶሎ ቶሎ መለዋወጥ አለመረጋጋት ወይንም ቁጡ መሆን ዘና ማለት አለመቻል ሁሉ ነገር ከአቅም በላይ የሆነ መስሎ
መሰማት የብቸኝነት ስሜትና እራስን ማግለል ድብርትና ደስተኛ አለመሆን አካላዊ ምልክቶች የህመም ስሜት የሆድ ድርቀት ማቅለሽለሽና ራስ ማዞር የደረት ህመምና ፈጣን የልብ ምት የባህሪ ምልክቶች ከመጠን በላይ ወይንም በታች መመገብ ብዙ ወይንም ትንሽ ሰዓት መተኛት እራስን ማግለልና ብቸኛ መሆን ኃላፊነትን ችላ ማለት አልኮሆል ሲጋራና መጠጥ ዘና ለማለት
መጠቀም ውጥረት የሚያመጡ ነገሮች በጣም ብዙ
ናቸው ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ
ችግር: የምንወዳቸው ሰዎች በሞት: መለየት
ከፍተኛ የስራ ጫና : የግኑኝነት ችግሮች :
ቤተሰብና ልጆች ለከፍተኛ ስትረስ
ሊያጋልጡን ይችላሉ :: እንደዚሁም ደግሞ እራሳችን በውስጣችን የምንፈጥራቸው
ነገሮች ለከፍተኛ ስትረስ ሊያጋልጡን
ይችላሉ ለምሳሌ እጅግ አብዝቶ መፍራት :
አሉታዊ አስተሳሰብ : እውነታ ላይ
ያልተመሰረተ ፍላጎትና መሻት : ድርቅ ያለ
አስተሳሰብ ጥቂቶቹ ናቸው :: ከመጠን ያለፈ ውጥረትን እንዴት መከላከል ይቻላል እያንዳንዱ ሰው ለውጥረት ያለው ምላሽ
የተለያየ በመሆኑ ለሁሉም ሰው
የሚያገለግል አንድ ወጥ የሆነ መፍትሄ
የለም :: ውጥረትን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት
አይቻልም ነገር ግን ወደ መደበኛው መጠን
በማውረድ ጤነኛ መሆን ይቻልል :: ለዚህ አራት መንገዶች አሉ ማስወገድ – አላስፈላጊ ስትረስን
ማስወገድ እንችላለን :: መጨነቅ
ያለብንንና የሌለብንን ነገሮች ለይተን
ማወቅ ያስፈልጋል የግድ መደረግ
ያለባቸውን ነገሮች ምርጫ ካላቸው
ነገሮች ለይተን ማወቅ አለብን ለምሳሌ አንድን ዕቃ ለመግዛት ገንዘብ አጥሮን
ጭንቀት ውስጥ ብንገባ በመጀመሪያ ያ
ዕቃ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው
ወይንስ አይደለም የሚለውን ማወቅ
አለብን ሌላ አማራጭ ካለን እቃውን
በሌላ በመተካት ወይንም እስከነአካቴው በማስወገድ በሱ
ምክንያት የሚመጣውን ጭንቀት
ማስወገድ እንችላለን :: መቀየር ወይም መለወጥ – ጭንቀትን
ያመጣውን ጉዳይ የግድ ማስወገድ
የማንችል ከሆነ ሁኔታውን ለመቀየር
መሞከር አለብን :: ለምሳሌ በአንድ
ጉዳይ ላይ እንደተቸገርን ለወዳጆቻችን
በማማከር የጭንቀት መጠኑን መቀነስ ይቻላል :: መላመድ – ስትረስ ከሚፈጥርብን
ነገር ጋር መላመድ መቻል : ፖዘቲቭ
በሆነው የህይወታችን ክፍል ላይ
ማተኮር : ለምሳሌ የምንሰራው ሥራ
ቢያስጨንቀን ከስራችን የምንወደው
ክፍል ላይ ማተኮር ይረዳል:: መቀበል – ልናስወግድ የማንችለውን
ነገር አምነን መቀበል አለብን :: ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ዘና የሚያደርጉንን
ነገሮች ማድረግ ስትረስን ይቀንሳል ::
|