እኛ
ኢትዮጵያውያን በጣም
የምንወደውን ነገር “እንደ
አይኔ ብሌን ነው
የምሳሳለት” እያልን መግለፅ እናዘወትራለን። እናም የዚህችን አለም
መጥፎውንም ሆነ ደጉን
የምንመለከትበትና
የምንሳሳለት አይናችን
በህይወት ዘመናችን
ሁሉን እንዲያሳየን ጥንቃቄ ልናደርግለትም
ይገባል። ስለሆነም ጤናማ አይን
እና የጎላ እይታ
እንዲኖረን ቀጥሎ
ከተዘረዘሩት መጥፎ
ልማዶች ብንርቅ
ይመከራል። የተወሰኑ ልማዶች እኛ
በውል ሳናውቃቸው
ነው በአይናችን ላይ
ጉዳት የሚያደርሱት። 1. ሲጋራ ማጨስ -
በሲጋራ ውስጥ ከ7 ሺህ
በላይ ኬሚካሎች አሉ።
እነዚህን ኬሚካሎች
ማጨስም አይናችንን
በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል። 2. ተንቀሳቃሽ ምስሎችን
ላፕቶፕ ወይም
ታብሌቶች ላይ
መመልከት -
ማንናውንም ነገር ወደ
ፊታችን በጣም አቅርበን መመልከት ለአይናችን
መጥፎ ነው። ለረዥም
ጊዜ ቴሌቪዥን
መመልከትም የእይታ
ችግር ይፈጥራል ነው
የተባለው። 3. የጸሀይ ብርሀን ጨረር
መከላከያ መነጽር
አለማድረግ - ለጸሀይ
ብርሀን ጨረር
በምንጋለጥባቸው
አካባቢዎች የጨረር መከላከያ መነጽር
ማድረግ
አልትራቫዮሌት ጨረር
በቀጥታ አይናችንን
እንዳይጎዳን ይረዳል። 4. ደማቅ ቀለም ያላቸው
ምግቦችን አለመውሰድ-
በፔክቲን የበለጸጉ እንደ
ካሮት ያሉ እና ለአይን
ጤና የሚመከሩ
ምግቦችን አለመውሰድ ለውዱ አይናችን
መስጠት የሚገባንን
ማጓደል ነው። 5. በተሽካርካሪ ውስጥ
እየተጓዙ ማንበብ -
አድካሚ እና አሰልቺ ጉዞ
ስናደርግ ከድብርት
ለመውጣት ስንል
መጽሃፍት እናነባለን፤ ይሁን እንጂ ይሄ ልማድ
ለአይናችን ጤና
መልካም አይደለም
ተብሏል። 6. በቂ እንቅልፍ
አለማግኘት 7. ኮምፒውተር ላይ
ረጅም ጊዜ የሚያጠፉ
ሰዎች አይናቸውን
በተወሰነ ደቂቃ ልዩነት
ማርገብገብ እንዳለባቸው
ይመከራል። ይሁን እንጂ ባለማወቅም
ይሁን በመርሳት
አይናችንን
ካለማርገብገብ የተነሳ
አይናችን ሊጎዳ
ይችላል። 8. አጥብቦ መመልከት -
የተለያዩ አጋጣሚዎች
አይናችንን አጥብበን
እንድንመለከት
ይጋብዙናል፤ ነገር ግን
ይህ ነገር እየተደጋገመ ሲመጣ እና ልማድ
ሲሆን ለአይናችን
በርካታ ጠንቆች ይዞ
እንደሚመጠ ነው
የሚነገረው። 9. በቂ ብርሃን
በሌለው ቦታ ማንበብ 10. መነጽር
እንዳደረግን መተኛትም
ለተለያዩ የአይን
ኢንፌክሽኖች
ያጋልጣል። ምንጭ:- http://
buynongmoseeds.com/
|