ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ሰውን አትናቅ
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - ሰውን አትናቅ
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
=> ከ ሴቶች እዉነታ
=> የቢልጌትስ አስገራሚ እውነታዎች :
=> የህይወት 5ቱ እውነታወች እውነታ
=> የየአገሩ ምሳሌያዊ አባባል
=> ሰውን አትናቅ
=> የጣቶን ነገር ያንብቡ
=> ኢትዮጵያን ልዩ የሚያደርጋት
=> ልብ ብለው ያንብቡት!! ሰውን አትናቅ .......!
=> የ10 ኣመት ህፃን ልጅ
=> 32
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
ልብ ብለው ያንብቡት!! ሰውን አትናቅ .......! አልበርት አንስታይን በዩኒቨርሲቲዎችና በየምርምር ተቋም እየዞረ ስለ ታወቂው አንፃራዊነት ቲዎሪ ሌክቸር ሲሰጥ ሁሌም አብሮት የሚሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው የታክሲ ሹፌር ( cab driver ) ነበረው። ሹፌሩ አነስታይን ሌክቸር ሲሰጥ በተደጋጋሚ ሰዎች በተመስጦ ሲያዳምጡ በማየቱ እሱም በትኩረት እና በተመስጦ እየተከታተለ ከሞላ ጎደል ፅንሰ ሐሳቡ በሚገባ ገብቶታል። አንድ ምሽት የተለመደውን ሌክቸር እንዲሰጥ አንስታይንን ይዞት እየሄደ ሳለ ባጋጣሚ አነስታይን ይታመማል ሹፌሩም "እንመለስና ወደ ሆስፒታል ልውሰድህ" ቢለው አንስታይንም" በፍፁም አይሆንም ባይሆን ሌክቸሩን ከሰጠሁ በኋላ ወደ ህክምና እሄዳለሁ" ብሎ እምቢ አለው። በዚህ ግዜ ሹፌሩም "ይህን ያህል ጊዜ አብረን ስንውል የምታስተምረውን ሌክቸሮች ከመከታተሌ ብዛት ሀሳቡ በሚገባ ስለገባኝ አንተን ተክቼ መስጠት ስለምችል አንተ አረፍ በልና እኔ ሌክቸሩን ልስጣቸው " ይለዋል። አንስታይንም በዛ ምሽት ሌክቸሩን በሚሰጥበት ቦታ በስም እንጂ ማንም በአካል እንደማያውቀው በማወቁ በሹፌሩ ሐሳብ ተስማማና ወደ ክፍሉ ገብቶ ጥጉን ይዞ ተቀመጠ። ሹፌሩም ራሱን አነስታይን ነኝ ብሎ በማስተዋወቅ ወደ ሌክቸሩ ገባ ጥሩም አድርጎ አስተምሮ ጨረሰ ተሰብሳቢውና የሳይንስ ተማሪዎቹ መርካታቸውን በጭብጨባ ገለጹ እሱም አመስግኖ ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል አንድ ኘሮፌሰር ቀረብ ብሎ ፈታኝ የሆነ ነገር ግን ሆን ብሎ ለማሳጣት የፊዚክስ ጥያቄ ጠየቀው። ሹፌሩም ምንም ሣይደናገጥ ጥቂት አሰብ አደረገና " ይሄ እኮ በጣም ቀላል ጥያቄ ነው በእርግጠኝነት ሹፌሬን ብትጠይቀው በአጥጋቢ መልኩ አብራርቶ ይመልስልሀል " በማለት በኩራት ለኘሮፌሰሩ መለሰለት ። ኘሮፌሰሩም ጥግ ላይ ተኮራምቶ የተቀመጠውን ሹፌር በንቀትና ፌዝ በተቀላቀለበት መልኩ ቢጠይቀው ሹፌሩም ( አነስታይንም) ከበቂ በላይ ሰፋ ባለ መልኩ አብራርቶ መለሰለት:: ኘሮፌሰሩም በጣም በመደናገጥና በመሸማቀቅ ጭንቅላቱን ደፍቶ በአግራሞት ምንም ነገር ሳይናገር ወጥቶ ሄደ። እናም በማናለብኝነት ራስን አግዝፎና ሰቅሎ በማስቀመጥ ሌላውን ደግሞ አሳንሶ መመልከት ያልታሰበ ውርደት ውስጥ ሊከትህ ስለሚችል ወዳጄ ሆይ ሰውን አትናቅ ማንም ቢሆን ምንጭ:- Janbo Jakov(ልብ ብለዉ ያንብቡት ja)
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free