ያለምንም ክፍያ የግሎን ሳይት ለመክፈት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ < እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - የጣቶን ነገር ያንብቡ
< እንኳን ወደ ኢትዮትሪክ ገጽ በደህና መጡ ! > - የጣቶን ነገር ያንብቡ
 
menu
የተለያዩ ተረቶች
ሳይት ጥቆማ
ቀልዳቀልዶች
የታዋቂ ሰዎችና የሌሎች ታሪክ
የተለያዪ መረጃዎች
ከመፅሀፍት አለም
እዉነታዎች
=> ከ ሴቶች እዉነታ
=> የቢልጌትስ አስገራሚ እውነታዎች :
=> የህይወት 5ቱ እውነታወች እውነታ
=> የየአገሩ ምሳሌያዊ አባባል
=> ሰውን አትናቅ
=> የጣቶን ነገር ያንብቡ
=> ኢትዮጵያን ልዩ የሚያደርጋት
=> ልብ ብለው ያንብቡት!! ሰውን አትናቅ .......!
=> የ10 ኣመት ህፃን ልጅ
=> 32
ግጥሞች
የሳይቱን አዘጋጁን ለማግኘት
ጤና አዳም
ከዘመኑ
የተለያዪ የሙዚቃና የመዝሙር ግጥሞች
ወቅታዊ ዜናዎች፦
መነሻ ገፅ
የእጅ ጣታችን ርዝመት ስለ ማንነታችን ወይም ባህሪያችን ይገልፅ ይሆን? ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ምስሎችም የቀለበት ጣታችንና ሌባ ጣታችን ያላቸውን ርዝመት በማነፃፀር ባህሪያቶቻችን ለማወቅ ያስችላሉ ተብሏል። ምስሎቹ በጣታችን ርዝመት መሰረት A, B እና C በሚል የተቀመጡ ሲሆን፥ እርስዎም የጣትዎን ርዝመት በመመልከት በየትኛው እንደሚመደብ ከለዩ በኋላ ከዚህ በታች የተቀመጡት መግለጫዎች ከተጨባጭ ማንነትዎ ጋር ይስማማሉ አልያም ይቃረናሉ የሚለውን እንዲመለከቱ ጋብዘናል። 1) "A" የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት መብለጡን የሚያሳይ ነው - ምስል “A”። በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የቆንጆ ተክለሰውነት ባለቤት መሆናቸው ይነገራል። ሌሎች ሊያገኙት የሚጓጉለትን ነገር በቀላሉ ለማግኘት እንደሚችሉም ነው መረጃው የሚያመላክተው። በተጨማሪም እጅግ በጣም ተናዳጅና ለውሳኔ የፈጠኑና አደጋን ለመቀበል የማይፈሩ ናቸው ተብሏል። አብዛኞቹ ወታደሮች፣ ኢንጂነሮችና ቼዝ ተጫዋቾች ሲሆኑ የቃላት ድርደራ ጨዋታዎችን በመጫዎት የሚያህላቸው የለም። የቀለበት ጣታቸው ከሌባ ጣታቸው የሚረዝም ሰዎች አጭር የቀለበት ጣት ካላቸው ሰዎች ይልቅ የተሻለ ገቢ እንደሚያገኙም ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል። 2) "B" በዚህ ምስል ላይ እንደምንመለከተው የቀለበት ጣት ከሌባ ጣት የሚያጥር ሲሆን፥ አጭር የቀለበት ጣት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ በራስ የመተማመን የተላበሱ መሆናቸው ይነገራል። ራስ ወዳድነትና ትእቢት ቢጤ የሚያጠቃቸው እንደሆኑም መረጃው ይገልፃል። ብቻቸውን መሆን የሚያስደስታቸው ሲሆን በእረፍት ስአታቸው መረበሽን አጥብቀው የሚጠሉ ናቸውም ተብሏል። በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት ይፈራሉ የተባሉት ይህ አይነት የጣት አወቃቀር ያላቸው ሰዎች፥ በሌሎች ሰዎች እይታ ውስጥ መግባትን ግን የሚያደንቁና በጣም የሚፈልጉ ናቸው። 3) "C" የቀለበት ጣትና የሌባ ጣት እኩል መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ሌባ ጣታቸውና የቀለበት ጣታቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ሰላም ወዳድ እና ፀብና አለመረጋጋት ባለበት ቦታ ድርሽ ማለት የማያሹ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ለነገሮች ትኩረት የሚሰጡና የተቀናጁ ሲሆኑ፥ ከበርካታ ሰዎች ጋር በቀላሉ የመግባባት ብቃት አላቸው። ለፍቅር ግንኙነትም ታማኝና ቅን ልቦና ያላቸው መሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ አመለ ሸጋና ለፍቅር አጋራቸው እንክብካቤ የሚያበዙና የሚጠነቀቁ አይነት ሰዎች ናቸው። እስኪ እርሶም ይሞክሩትና ማንነትዎን ይገልፃል አይገልፅም የሚለውን ያረጋግጡ። ኤፍ.ቢ.ሲ ምንጭ፦ http://www.healthylifetricks.com/ ተተርጉሞ የተጫነው፦ በፋሲካው ታደሰ
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free