1.ቢልጌትስ በየሰከንዱ
250 ዶላር፣በየቀኑ 2
ሚሊዮን ዶላር፣በአመት ደግሞ 7.8 ቢሊዮን ዶላር ያገኛል፡፡
2.አንድ ሺ ዶላር
መሬት ላይ ቢወድቅበት
ዞር ብሎ እንኳን
ለማየት ግድ አይኖረውም ይባላል፡፡ምክንያቱም
የወደቀበትን ገንዘብ ለማንሳት የሚያጎነብስበት
አራት ሰከንድ ጊዜው
ውስጥ አንድ ሺ ዶላር
ስለሚያገኝ ነው፡፡ 3.የአሜሪካ ብሄራዊ እዳ
5.62 ትሪሊየን
ይደርሳል፡፡ ቢል ጌትስ ይህን እዳ ለብቻዬ
ልክፈል ብሎ ቢነሳ
ከ10 አመት ያነሰ ጊዜ ይፈጅበታል፡፡
4.ቢል ጌትስ በአለም
ላይ ለሚኖር
ለእያንዳንዱ ሰው 15 ዶላር ቢሰጥ በእጁ ላይ
5 ሚሊየን ዶላር ይቀረዋል፡፡
5.በአሜሪካ የአትሌት
ክፍያ ታሪክ ከፍተኛ
ተከፋይ የነበረው
ማይክል ጆርዳን ሳይበላና ሳይጠጣ በአመት የሚያገኛትን 30
ሚሊዮን ዶላር
እያንዳንዷን ሳንቲም
ቢያስቀምጥ የቢል
ጌትስን የመሰለ ሃብት
ለማጠራቀም 277 አመታትን ይፈጅበታል ተብሏል፡፡
6.ቢል ጌትስ ሀገር
ቢሆን ኖሮ የአለማችን
37ኛ ሃብታም ሃገር
ሊሆን ይችል ነበር፡፡ 7.ቢልጌትስ ያለውን
ገንዘብ በሙሉ በባለ 1 ዶላር ኖት
ቢመነዝረው፣ከምድር
እስከ ጨረቃ የሚደርስ
14 መስመር የደርሶ መልስ መንገድ መስራት
ይችላል፡፡ ነገር ግን
ገንዘቡን በማመላለስ ይህን መንገድ
ለመገንባት 1400
አመታት እና 713 ቦይንግ 747
አውሮፕላኖች
ያስፈልጋሉ፡፡
8.ቢል ጌትስ እስከ 75 አመት ድረስ ለመኖር
ቢታደልና ገንዘቡን በሙሉ ከዕለተ ሞቱ
በፊት ተጠቅሞ
ይጨርሰው ቢባል በየቀኑ
6.78 ሚሊዮን ዶላር
ማውጣት ይኖርበት ነበር፡፡ 9.የማይክሮሶፍት
ተጠቃሚዎች
ኮምፒውተሮቻቸው
በwindows ችግር
የተነሳ ስራ
በሚየቆሙበት በእያንዳዱ ወቅት አንድ ዶላር ከማይክሮሶፍት
ቢከፈላቸው ኖሮ
ቢልጌትስ በሶስት
አመታት ውስጥ ለኪሳራ
ይዳረግ ነበር፡
|