ሚስት ባሏን በስጨት ለማድረግ አስባ መኝታ
ክፍል ትገባና አጭር ደብዳቤ ፅፋለት ከእልጋ ስር
ትደበቃለች። ባል ከስራ መጥቶ "አቤት" የሚለው
ሲያጣ መኝታ
ክፍል ልትሆን ትችላለች ብሎ ሲገባ ደብዳቤውን
ያገኝና ማንበብ ይጀምራል። እንዲህ ይላል፦ "ሌላ ሰው አፍቅሬያለሁ። አንተ
በቅተከኛል። ቻው!" ባል ፈገግ ይልና ስልኩን
አንስቶ፦ "ሄሎ የኔ ቆንጆ። አይገርምም ያቺ የዋህ
ሚስቴ በራሷ
ጊዜ ወጥታ ጠፍታለች። በቃ መጣሁ ጠብቂኝ።"
ብሎ ይወጣል። ሚስት እያለቀሰች ከተደበቀችበት ስትወጣ አልጋው
ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀምጧል። አንስታ ስታነበው
እንዲህ ይላል፦ "ከአልጋው ስር መሆንሽን
አውቃለሁ። አሁን
የወጣሁት ወይን ገዝቼ ልመጣ ነው። ስመለስ ቆንጆ
ራት ሰርተሽ ጠብቂኝ የኔ ማር። እወድሻለሁ!!!"
|