አንድ ታካሚ ከባድ የሆነ የወገብ አደጋ ደርሶበት
ዶክተር ጋር በጠዋቱ ይመጣል:- ዶ/ር:- "ወገብህ
እንዲህ እስኪሆን ድረስ ምን ገጥሞህ ነው?" ታካሚ:-
"ይሄወልህ ዶክተርዬ ስራዬ ሌሊት ነው ታዲያ ዛሬ
ጠዋት ኮንዶሚኒዬም ቤታችን ስገባ መኝታ ቤት
ከሚስቴ ጋር የሆነ ሰው ሲያንኮሻኩሽ ሰማሁኝ: መኝታ ቤቱን ከፍቼ ዘው ብዬ ስገባ ሚስቴ ብቻ ነው ያለችው:
የቤቱ ሁኔታ ግን የሆነ ሰው እንደነበረ ያስታውቃል:
ከመኝታ ቤት ወጣሁና በረንዳው ላይ ሆኜ ወደታች
ስመለከት የሆነ ሰው ሱሪውን እየታጠቀ ሲሮጥ አየሁኝ
ዶክተርዬ በጣም ተናድጄ ስለነበር ሳሎን ያለውን ፍሪጅ
አንስቼ ወረወርኩበት: ያንን ከባድ ፍሪጅ ሳነሳ ነበር ታዲያ ወገቤን ያመመኝ"ዶክተሩ ይሄን ታካሚ ካከመ
በሁዋላ ሌላ ታካሚ መኪና የተገጨ በሚመስል ሁኔታ
ሰውነቱ ቆሳስሎ ይገባል:- ዶ/ር:-በጌታ የመጀመሪያው
ታካሚዬ ሲገርመኝ ያንተ ደግሞ ባሰ! ምን ሆነህ ነው?
ታካሚ 2:- "ይሄውልህ ዶክተር ዛሬ አዲሱን ስራዬን
የምጀምርበት ቀን ነበር ድንገት አርፍጄ ተነሳሁኝና ከቤቴ ስወጣ ሱሪዬን እየለባበስኩኝ እየሮጥኩ እያለ
ከየት መጣ ያላልኩት ፍሪጅ ላዬ ላይ ወደቀብኝ!"
ዶክተሩ ይሄንንም አክሞ ከሸኘ በሁዋላ ሌላ ታካሚ
ይገባል:- ይሄኛው ታካሚ ደግሞ ከሁለቱ በባሰ እና
በሚዘገንን ሁኔታ ቆሳስሎ ነበር የገባው:- ዶ/ር:- ኧረ ዛሬ
ምን አይነት ቀን ነው!? አንተ ደግም ምን ሆነህ ነው? ታካሚ 3:- "ዶክተር ለምን? እንዴት? ማን? ብለህ
እንዳትጠይቀኝ: ዛሬ ጠዋት ፍሪጅ ውስጥ ገብቼ እያለ
ከፎቅ ላይ ተከስክሼ ነው!"
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
|