አንድ የእምነት ሰው ፀጉሩን
ሊስተካከል ወደ አንድ ፀጉር አስተካካይ ቤት
ይሔዳል እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል
ፀጉር_አስተካካይ : 'ታውቃለህ ፈጣሪ የለም !'
ተስተካካይ: በመገረም) 'እንዴት' ?
አስተካካይ : 'አይታይህም '? ተስተካካይ : 'ምኑ '? አስተካካይ : 'እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ
ጦርነት ፣ረሀብ ፣ችግር ፣ስርአት
አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ ፈጣሪ አንዴ
ፈጥሮን ትቶን ሔዷል ወይ ሞቷል' ።
ተስተካካይ : 'ታውቃለህ ፀጉር አስተካካይ የሚባል
የለም' አስተካካይ : ( ግራበመጋባትና እንዲሁም
በመገረም) 'እንዴት'?
ተስተካካይ :'ፀጉር አስተካካይ ቢኖርማ ፀጉሩ
የጎፈረ ፂሙ የተንዠረገገ ሰው አይኖርም ነበር' ።
አስተካካይ : 'እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ፀጉር አስተካካይ
አለመምጣታቸው ነው እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ፀጉሩ የተንዠረገገ እና የተንጨበረረ
ፀጉር አታይም ነበር'
ተስተካካይ :'ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው
ችግርም ይኸው ነው ሰው ከፈጣሪው
ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም'።
|