አባት:- ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ
ማስቲካ
ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም? ክብረቢስ
ጎረምሳው:-ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ
እንዳይሸት
ብዬ ነው አባት:-ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ? ጎረምሳው:-
አዎ ግን አልፎ አልፎ ናይት ክለብ ስሄድ
ብቻ ነው
ምጠጣው
አባት:-ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ?!! አታፍርም እንዴ
ልጄን ለመጠየቅ ስትመጣ? ጎረምሳው:-ከእስር ቤት ስወጣ
ነው መሄድ የጀመርኩት
እንጂ
በፊት አልሄድም ነበር
አባት:-የባሰ አታምጣ!!!አንተ ሌባ ልጄን ሰርቀህ
ልታበላት ነው እንዴ? ጎረምሳው:-ሌባ አይደለሁም ሰው ገድዬ
ነው እስር ቤት
የገባሁት
አባት:-ምን!!!! ነብሰ ገዳይ ነህ?
ጎረምሳው:-አይደለሁም የዛን ቀን በጣም ተናድጄ
ስለነበር ነው ሰውየው የኛ ጎረቤት ነበር ልጁን ለማግባት
ጠይቄው ከለከለኝ
ከዛ ገደልኩት::
አባት:-ና እስቲ ልጄ ና እቀፈኝ ለልጄ እንዳንተ
አይነት
ጥሩ ባል ነበር ስፈልግ የነበረው
|