የዩንቨርስቲ ላይብረሪ ውስጥ ነው፣ ልጁ ወደ ልጅቷ
ጠጋ ይልና:
"እሙ እዚህ ጋር ብቀመጥ ቅር ይልሻል?" ይላታል፣
ልጅቷም ከመቀመጫዋ
ብድግ በማለት ድምጿን ከፍ አድርጋ: "እኔ
እንደ...... ማንም ተራ ሴት መሰልኩህ አብረሺኝ እደሪ የምትለኝ?!" ትልና ቁጭ
ትላለች፣ ይሄኔ
ላይብረሪ ውስጥ የነበሩት ተማሪዎች በግርምት ልጁ
ላይ ያፈጡበታል!
ልጁም በሃፍረት እና በመሸማቀቅ ቀስ ብሎ አጠገቧ
ይቀመጣል፣ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ልጅቷ ወደ ልጁ ጆሮ ጠጋ ብላ:
"አየህ..የስነ-ልቦና
ተማሪ ስለሆንኩኝ ወንድ ልጅን ማሸማቀቅ
አውቅበታለሁ!" ትለዋለች:
ልጁም ወዲያውኑ ከመቀመጫው ብድግ አለና ጮክ
ብሎ: "ለ አንድ አዳር አምስት ሺ ብር!? አልበዛም!? ፌር አይደለም!"
ይልና ቁጭ ይላል፣
በዚህ ጊዜ ላይብረሪ ውስጥ የነበረው ተማሪ እሷ ላይ
ያፈጣል: ልጅቷም
በሃፍረት ኩም ብላ አንገቷን ታቀረቅራለች: ይሄኔ
ልጁ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ይልና: "አየሽ.... የህግ ተማሪ ስለሆንኩኝ ሴትን ልጅ
ወንጀለኛ
ማድረግ አውቅበታለሁ" ብሎ ጥሏት ውልቅ!
|