መዝገበ ቃላት ወ ዘመኑ 1.የኛ ቡድን----አርሰናል/ ሊቨርፑል/ ቸልሲ/ባርሴሎና
2.በጭቅ ----ብር ስጠኝ 3.አስበኧዋል----ኮረዳዎቻችን
በየመሃሉ ጣል የሚያደርጓት አዝማች 4.ፖዝ አረገ----
ፈዞ ቀረ 5.በካ----በቃ 6.ንካው----ሂድ
7.አይገርምክም----አይገርምህም 8.ሰርፕራይዝ----
ህልመ ምዕራባዊያን የሆኑ እንስቶች ልብ የሚያደርቁበት ቃል 9.ሰጠኝ----“F” እና “D” ያመጣ ተማሪ አገኘሁ
ላለማለት የሚጠቀምበት 10.ሜንጫ----ፌስቡክ ላይ
ያሉ ሰነፎች የሚያስፈራሩበት ጉም 11.አንቺ----
ለወንድም ሆነ ለሴት እንደየሁኔታው የሚያገለግል
(የምታገለግል) መጠሪያ 12.አይ እሷ----አውሮፓ
ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ኳስ ተጫዋቾች የሚቆላመጡበት 13.ሼ ነው----ያሳፍራል 14.ፐብሊክ አድርገው----
አታሾክሹክ 15.የኛ አስታዲዬም (በኛ ሜዳ)----ፍላይ
ኢምሬትስ/ ኦልድ ትራ ፎርድ/ ሳንቲያጎ በርናባው 16.ዩ
ኖው----የአይዶል ዳኞች ዘፋኙን ሊያወዛግቡ ሲሉ
የሚጠቀሙበት መግቢያ 17.ላሞ----ሎል የፋራ ነው
የሚሉ ቆየት ያሉ ፌስቡከኞች ስቂያለው ለማለት የሚጠቀሙበት 18.በተረፈ ሰላም ነው----ደዋይ ቻው
ለማለት ሲከብደው የሚጠቀምበት ቻይንኛ
19.እስፖንዳ----የሴት ልጅ መቀመጫ
20.እስፖኪዮ----ፊት (በተለይ የሴት) 21.ብትጠራው
አይሰማህም---- አንድ ሰው በጣም ሃብታም ነው
ለማለት 22.ቀዩን ተጫነው----ስልኩን ዝጋው/ከፊቴ ዞር በል 23.እህ ገባ/ ኧረ ገባ ወይ----እያንቀላፉ
ያሉወጣቶች ምግባቸውን (ጫትን) በጉጉት
የሚጠባበቁበት የጠራራ ፀሃይ ጥያቄ 24.ፒን
እንውጋ----አረቄ እንጠጣ 25.እንያዝበት----እንቃም
26.የገባው/የገባት----ጫት የሚቅም/የምትቅም
የሚጠጣ/የምትጠጣ የሚዳራ/የምትዳራ 27.ገገማ---- ከገባው/ከገባት በቃራኒ ያሉ 28.እርዝራዥ----
የማይፈለገው/ የቀድሞው/ የተጣለው አባል/አካል
29.ዶክተር ኢንጅነር----የንግድ ስም 30.ሸኖ
እንበርግድ----ሽንት እንሽና 31.ቫይበር የለህም?----
ላንተ ገንዘብ አውጥቼ አልደውልም የሚለው አረፍተ
ነገር ምትክ 32.ሻወር እንብላ----ገላችንን እንታጠብ 33.ኮካ----ኮተታም ካድሬ 34.አሸባሪ----
ጋዜጠኛ፣ብሎገር/ጦማሪ፣የሃይማኖት/የፖለቲካ መሪ
35.ዋው፣ላላ፣ስቲል እስካሁን፣አይ
ስዌር፣አሜዚንግ፣ፕሊስ፣ታንኪው፣ፓራዶክስ፣ሪሊ፣ኦኬ፣
ኦ ማይ ጋድ----ዲያስፖራና ትምህርት ቀመስ
ላሜቦራዎች የሚጠቀሙት ሳውንድ ትራክ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
|