ለፈገግታ
ልጁ በመምህሩ ስድብ ተማረረ...
አንድ ቀን ወደ ቤት ሲመለስ ለአባቱ ነገራቸው
"አባዬ ሂሳብ አስተማሪያችን ሁል ጊዜ ደደብ
እያለ ይሰድበኛል"
አባት በንዴት "ይህን ሁሉ ገንዘብ እየከፈልኩ እንዴት እንደዚህ ይስድብሃል ነገውኑ ሄጄ
አናግረዋለሁ"
በነጋታው ወደ ት/ቤት አብረው ሄዱ..
አባት፡ በት/ቤቱ ዳይሬክተር ቢሮ
አስተማሪውን አስጠርቶ ማናገር ጀመረ
"ለምንድነው ልጄን ደደብ እያልክ የምትሰድበው?" መምህር፡ አዝናለሁ ልጆት በጣም ደደብ ነው"
አባት፡ በጣም ተናደው "አሁንም ደገምከው
እኮ"
መምህር: አይቆጡ ማስረጃ ማቅረብ
እችላለሁ" አባት: "ምንድነው ማስረጃህ?"
መምህር: "ና እስኪ አንተ ደደብ እዛ ክፍል ሄደህ እኔ እንዳለሁና እንደሌለው አይተህ ና"
ልጁ እየሮጠ ሄዶ መጣና "የሉም ቲቸር"
አባት: በንዴት "እውነትም ደደብ። የሉም ትላለህ
እንዴ? ሌሎች_ክፍሎች_ዞር_ዞር_ብለህ_
አታይም"
|