የሆነ አገር ውስጥ ነው አሉ፡፡ ባል እና ሚስት ሬድዮ
እያዳመጡ እያሉ መንግስት ከ5 ልጅ በላይ ላላቸው
ዜጎቹ በየወሩ የሚሰጥ ጠቀም ያለ ጉርሻ እንዳዘጋጀ
ይሰማሉ፡፡ ባልም ፈጠን ብሎ ለሚስቱ “ይቅር በይኝ
እናትዬ
፤ግን ከቀድሞ እጮኛዬ የወለድኩት የ14 አመት ልጅ አለኝ፤ እስከዛሬ ፈርቼሽ አልነገርኩሽም ነበር
፤አሁን ግን ገንዘቡም ስለሚያስፈልገን ይዤው
ልምጣና ከ4ቱ ልጆቻቸን ጋር አስመዝግበነው
ገንዘብ እንቀብልበታለን” ብሎ ይማፀናታል፡፡
ሚስትም ትንሽ ብትደናገጥም ከጥቂት ማቅማማት
በሗላ ሀሳቡን ስለተቀበለችው ልጁን ይዞ ሊመጣ ይሄዳል:: ከጥቂት ሰአታት በሗላ አባት
የውሽማውን ልጅ
ይዞ እየከነፈ ሲመጣ ቤት ውስጥ ሚስቱና አንድ
ልጁ ብቻ መኖራቸውን በማስተዋሉ ሌሎቹ ልጆች
የት ገቡ? ብሎ ይጠይቃል፡፡ ሚስትም ኮራ ብላ
ማስታወቅያውን አንተ ብቻ መሰለህ እንዴ የሰማኸው? አባቶቻቸው ይዘዋቸው
ሄዱአ
|