ማጣቱ ዘልቆ ሳይጎዳኝ፣ ድህነቱን ችየ በኖርኩኝ፣ እህ ብየ ተመስገን ብየ ኑሮ በገፋሁኝ፣ የመኖሬን ተስፋ ቀማችሁኝ፣ ልጀን ወዳጀን ነጠቃችሁኝ፣ ደጋፊየ ጠዋሪየን በግፍ ቀማችሁኝ! እኔማ .... ደካማ እናት ነኝ፣ ልጀን በጨካኞች በግፍ ያጣሁኝ፣ አሳቢ ልጀን የተቀማሁ፣ የጎደለብኝ፣ እኔማ ዕድሜ ጠገብ፣ ደከማ ነኝ፣ ለበቀል የሚሆን ጉልበት የከዳኝ፣ የተገፊ እናት ነኝ፣ ኀዘን ጠልቆ የተሰማኝ፣ አዎ! አቅም ያጣሁ ምንዱብ እናት ነኝ! ብቻ ተስፋየ በሱ ነው፣ በማይተወኝ፣ የፈጠረኝ መድኃኒዓለም ይፋረደኝ፣ በቀል አይቀርም ተስፋ አለኝ! እሱ አንድየ ይድረስልኝ! መድኃኒዓለም ይፋረደኝ! አዎ! እናታለም፣ መድኃኒዓለም ይፋረደን!!! አዎ! እናት ዓለም ... የበቀል አምላክ ዝም አይልም፣ መድኃኒዓለም ይፈርዳልም! ነቢዩ ሲራክ በጨለመው ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም
|