ምን ያለ ዘመን ነው ተወግዞ ያስወገዘ የሰው ደም ቀዝቅዞ ለውሃ ያገዘ እንስሳ መሰሉን ሲበላ አላየሁም ሰው ሰውን ለመብላት ምነው አላቅማማም? ለምን ማረድ? ቢሉት አለው ወይ አንደበት ጉልበቱን ገትሮ ደም ከንቱ የደፋበት ግፍ ይቆጥራል በለው ሥራ ይቆጥራል በለው ከላይ የነፍሱ ባለቤት አይቶም እንዳላየ ዝም ያለ
እንዳይመስለው። ሺ ብታነብበት እውቀትህ ቢሰፋ ግፍህን ይቆጥራል ደካማን ሥትገፋ ለቋሚ ነው እንጂ ድንፋታህ የሚሰማ ነፍሱን ለለየሃት ደሙን ላፈሰስከው አንተ ነህ ደካማ። ይህ የጣልከው ምስኪን ታሪኩን ሰምተሃል? የሚስኪኑን እናት ኑሮዋን አይተሃል? ፍሬም አላገኘህ ሃራም ነፍስ ገፍተሃል! ከፈጣሪ በላይ ማን ይፋረድሃል?! ይህ የጣልከው ምስኪን ታሪኩን ሰምተሃል? ድህነት ብቻ እንጂ ምን ክፉ ሠርቶሃል? የነ ነጋሺ ነው የነ ቢላል ዘር ነው ልቡ እምነት የሞላው አንተ የማታየው። ኑሮ ያባረረው ሕይወቱ ተማራ ቢሆንልኝ ብሎ የመጣው ይህ ሥፍራ! የፈጣሪን መሬት ስፋቱን በማየት ብሻገር ብሎ ነው ኑሮን ለማሸነፍ በፈጠረው እምነት። ሥራህ ቀደመብህ ተው ቢሉህ አትተው መቸም የለህ አንገት ዞራ አርገህ አታየው። ካረመኔው ግብር መች አልፎ ይህ ሥራህ ፋሽስት ከሠራው መች ከላማው ወጣህ። ሰው እንዲህ ረክሶ በግርህ ረገጥኸው? ደም እንዲህ ረክሶ ከባህር ደፋኸው? ደም ከንቱ ይቀራል ብለህ አትተኛ ከላይ አይቶብሃል የዓለሙ ዳኛ ደም ቢሉህ!!!! ያውም ለውነት ቋሚ ከመቸገር በቀር የሌለው አበሳ የኢትዮጵያን ልጅ በመልካም ነገር ላይ ታሪኩ የሚወሳ!
|