ሰኔ እና ሰኞ!
~~~~~~~~~~
አንዱ ከዛ ማዶ;
ይዞ መጣ መርዶ::
ሌላው ከዛኛው ጥግ;
ፊት የሚያስጨፈግግ; ይዞ ስለመጣ.....; ቀኑ አይን አወጣ;
ብለው ተቀኙና;
የድሮ አባቶች:
ለቅኔው ትርጉም ፍች;
ብሂል አቆዩልን:: ከችግር ጋራ ቀን;
ድንገት ቢገጥምብን; እንደዚህ እንድንል;....
ሀምሌ ከማክሰኞ;
መስከረም ከእሁድ;
ሺህ ጌዜ ቢዋደድ; ምንም አይመጣብን::
ግራ ከ ግራ ጋር;
ባንድ ሲጫንብን; አንደፊተኞቹ እንዳባቶቻችን;
ሰኔ ከ ሰኞ ጋር;
ገጠመብን አልን:: ~~~~~~~~~~~~~
©ሃይላት!
ሰኔ 1 ሰኞ 2007ዓም.
|