ይድረስ ለገፀ-ባህሪው. . . ግባ በለው አሉ አልሰሜን
ከበሩ
ያልተገለጠለት ያልገባው ሚስጥሩ
የየት ዘመን ሰው ነህ የየትስ ሀገር ሰው
እንደ አክሱም ሃውልት ሰው
የምትጠብቀው አልሰማህም እንዴ የዘንድሮ ፍቅር እንደ ሐምሌ
ንፋስ እንደ ጠዋት ጀንበር
ሽው እልም ፉ ብልጭ ብሎ
እንደሚሰውር
ቆመህ ስትጠብቃት እንደ ላሊበላ
ቀድማ ካገኘችው ሄዳለች ከሌላ ወዳጄ ልምከርህ ጆሮ ካለህ ስማ ምታወራው ፍቅር
ዘንድሮ የለማ
አንተም እዛው ቆመህ ሃውልት ሳትባል
ተንቀሳቀስና ካንዷ ጋር ተሸብለል
አለበለዚያ ግን ከላሊበላና ካክሱም
ተደርበህ ታሪክ ማስተማሪያ መፅሐፍ ትሆናለህ (ልዑል
እንዳልካቸው)
|