ልጅ ባልቴት እናቱና
በቅርብ ያገባት ቆንጆ ሚስቱ አልስማማ ብለውት
ተቸግሯል . . . ለማስማማት ቢጥርም መልሶ
ነገራቸው እያገረሸ ሰላሙን ነሳው . . . ሚስቱ ታዲያ
አንድ ቀን እንዲህ አለችው ‹‹ ስማ ካሁን በላይ
አብሬህ አልኖርም ይች ባልቴት እናትህ እየነተረከችኝ እየሰደበችኝ አልኖረም …..ልጅ
ታዲያ ቢመክር ቢዘክር በእርጅና ምክንያት አልሰማ
ያለችው እናቱን አንከብክቦ አዘለና ጥቅጥቅ ወዳለ
ጫካ ጉዞ ጀመረ በቃ የሚወዳት ስንቱ የሚመኛት
ቆንጆ ሚስቱን ከማጣት እድሜዋን የጨረሰች
እናቱን ሊጥላት ወሰነ . . . ታዲያ በጫካው ውስጥ ሲሄድ እናት ልጇ ጀርባ ላይ ሁና ቅጠል እየበጠሰች
ትጥል ነበር . . . የጫካው ጥልቅ ቦታ ላይ ሲደርስ
እንዲህ አለ ‹‹ ደህና ሁኝ እናቴ ከዚህ በላይ መታገስ
አልችልም ›› በቃ ዞሮ ሳያያት እናቱን ጥሎ ተመለሰ
ጫካው ውስጥ ተደብቆ ይህን ነገር ሲመለከት የነበረ
አዳኝ ታዲያ ወደተጣለችው ናት ጠጋ አለና ‹‹ከመነሻው ጀምሮ ስከተላችሁ ነበር ልጅሽ
ሊጥልሽ ሲመጣ ጀርባው ላይ ሁነሽ በየመንገዱ
ቅጠል እየበጠሸ ስትጥይ የነበረው ለምን ነበር ››
ሲል ባልቴቷን እናት ጠየቃት
መልሷ አጭር ነበር ‹‹ ልጀ እዚህ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ
ውስጥ እኔን ጥሎ ሲመለስ መንገዱ እንዳይጠፋበት ብየ ነው!
|