በድብቅ ስወድሽ
******//******
በ'ህት ወንድምነት የጀመርነው ቅርበት
በጊዜ እርዝማኔ መላመድ ነግሶበት
ሳላውቀው በሒደት ስር እየሰደደ
መልካም ሴትነትሽ ውስጤ እየነደደ በተፈጥሮሽ ማማር በልዩ ሁኔታሽ
በቁምነገር ለዛሽ በቀልድ ጨዋታሽ
ከሆዴ ተኝተሽ ተገዝግዞ አንጀቴ
ልቤን ከሰረቅሽኝ ቆይተሻል እቴ
ግን ለኔ ያለሽን ጥሩ ስሜትሽን
እንዳላጣው ብዬ እህትነትሽን ስሸኝ ስቀበልሽ ዘወትር ባይኖቼ
መውደዴን ለመግለፅ ቃላቱን ፈርቼ
ከሌላ ጋር ሆነሽ ስቀሽ ስትላፊ
ውስጤ እየቆሰለ በቅናት እላፊ
ባገኘሁሽ ቁጥር እህት አለሜ ስል
አርሬ እየደበንኩ የግዴን ሳስመስል አንቺም ሳትረጂኝ ወንድሜ እያልሽኝ
እኔም ሳልናገር ጨርሶ እንዳትሸሺኝ
በዝምታ ቀንበር በፍቅርሽ ስታረስ
አለሁኝ አንድ ቀን እስኪገባሽ ድረስ
.....
......ከናቲ
|