ከሰው ይልቅ ለኔ
""""""//"""""
ከሰው ሰው ተወልጀ
የሰው ልጅ ሲጥለኝ
ላይኑ ተፀይፎ ሲያልፈኝ
በእጁ መንካት ሲጠየፈኝ አምላክግን አልጣለኝ
ከሰው ልጆችየተሻለ
ታማኝ ጓደኞች ሰጠኝ
ተመስገን ልበለው እንጅ
በምድር እያለሁ ተገልየ
ከታዘብኩ የሰውነን ልጅ ተመስገን አሁንም ጌታየ
ልብስ ባይኖረኝም እንደሰው
ባያድለኝ ቤትና መኪና
ባይኖረኝም ጌጣጌጥ
ማብለጨልጭ ማጌጠው
አሀሁንም ተመስገን አምላኬ ከሰው ከተሻለ ጓደኛየ ለኔ
እንደሰው ባልኖርስ ለምኔ
አዝኝ ሩሁሩህ ካልሆንኩኝ
እንኳንም እንደሰው አልኖርኩኝ
ለናንተ ይብላ ኝ እንጅ እኔስ
ምኮራባቸውታማኝ ጓደኞች አሉኝ ሲበሉምሲጠጡ ማይነጥሉኝ
ለሰላምታእንኳን ማይጠየፉኝ
ስንሄድ ስንተኛማያገሉኝ አሉኝ
አሉኝ ጓደኞችተመስገን ልበል
ሰውሆኘእንደሰውሰውንከማግለል
በሰው ጨክኘሰውን ከምጥል እየበላሁ ሲራቡ ከምስቅ
ለብሸ በተራቆቱት ከምሳለቅ
እንኳንም አልኖርኩ እንደሰው
አሁንም ተመስገን ልበለው
ለናንተ ይብላኝ ይብላኝ
አምላክ ጥሎ አልጣለኝ ታማኝ ጓደኞች ሰጠኝ
መቸም ማልከዳቸው ማይከዱኝ
እንደሰው ማይጠየፉኝ
ይብላኝ ይብላኝ ለናንተ
አመላኬ ታላቅምስጋና ላንተ
ከሰው ይልቅ ለኔ አዛኝ ሩርሩህ ጓደኞች ስለሰጠኸኝ።
""""""""""//"""""""""
ነብያት
|